





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከሙዓዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ጉዞ ላይ ነበርኩ። አንድ እለት እየተጓዝን ሳለ ወደርሳቸው ቀረብኩኝና እንዲህ አልኳቸው: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝና ከእሳትም የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ?" እርሳቸውም " በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው። አላህን ልትገዛና በርሱ ላይ ምንንም ላታጋራ፤ ሶላትን ቀጥ ልታደርግ (በአግባቡ ልትሰግድ)፤ ዘካን ልትሰጥ፤ ረመዳንን ልትጾም፤ የአላህንም ቤት ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉና ቀጥለውም እንዲህ አሉ: "የመልካም ነገሮችን በር አልጠቁምህምን? ጾም ጋሻ ነው፤ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሁሉ ምፅዋትም ወንጀልን ታጠፋለች፤ የሰውዬው በሌሊቱ አጋማሽ የሚሰግደው ሶላት" አሉና ቀጥለው {ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ} ከሚለው {ይሰሩትም በነበሩት} እስከሚለው ድረስ [ሱረቱ ሰጅዳ: 16‐17] አነበቡ። ቀጥለውም "የነገሩ ሁሉ ራስ፣ ምሰሶውንና ሻኛውን ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልኳቸው። እርሳቸውም "የነገሮች ሁሉ ራስ (ዋና) እስልምና ነው፤ ምሰሶው ሶላት ነው፤ ሻኛው ጂሃድ ነው።" አሉ። ቀጥለውም "ይህን ሁሉ የሚቆጣጠረውን ነገር ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ ነቢይ ሆይ!" አልኳቸው። ምላሳቸውን ያዙና "በራስህ ላይ ይህቺን ቆጥባት!" አሉ። እኔም "የአላህ ነቢይ ሆይ! እኛ በምንናገረው እንያዛለንን?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ትጣህና ሙዓዝ ሆይ! ምላሳቸው ያጨደችው ካልሆነ በቀር ሰዎችን በፊታቸው ወይም በአፍጢማቸው እሳት ውስጥ የሚደፋቸው (ሌላ ነገር) አለ እንዴ?" አሉኝ።»
ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።ሙዓዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ጉዞ ላይ ነበርኩ። አንድ እለት እየተጓዝን ሳለ ወደርሳቸው ቀረብ አልኩኝና እንዲህ አልኳቸው: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝና ከእሳትም የሚያርቀኝን ስራ ይንገሩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: በነፍስ ላይ መስራቱ ከባድ ስለሆነ ስራ ነው የጠየቅከኝ። አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ግን ገርና ቀላል ነው። የእስልምናን ግዴታዎች ፈፅም: የመጀመሪያው: አላህን በብቸኝነት መገዛትና በርሱም አንዳችን አታጋራ፤ ሁለተኛው: በቀንና ምሽት አምስቱን ግዴታ ሶላቶች: ፈጅር፣ ዙህር፣ ዐስር፣ መግሪብና ዒሻን መስፈርታቸውን፣ ማዕዘናቸውንና ግዴታዎቻቸውን አሟልተህ ቀጥ አድርገህ መስገድ ነው፤ ሶስተኛው: ግዴታ የሆነብህን ዘካ ማውጣት ነው: ይህም ገንዘብ በሸሪዓ የተገደበን መጠን በደረሰ ጊዜ ለሚገባው አካል የሚሰጥ በሁሉም ገንዘብ ላይ ግዴታ የሆነ ገንዘባዊ አምልኮ ነው፤ አራተኛው: ረመዳንን ትጾማለህ: እርሱም አምልኮን በመነየት ጎህ ከወጣችበት ወቅት ጀምሮ ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ከመብላት፣ ከመጠጣትና ከሌሎችም የሚያስፈጥሩ ነገሮችም መቆጠብ ነው። አምስተኛው: የሐጅ አምልኮን ለመተግበር አላህን ለማምለክ መካን በማሰብ የአላህን ቤት ሐጅ ማድረግ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ወደ መልካም በሮች የሚያደርስ መንገድ አላሳውቅህምን? ይህም እነዚህን ግዴታዎችና ሱና ተግባራትን በመከተል ነው: የመጀመሪያው: ሱና ጾም መጾም ነው። ይህም ስሜትን በመስበርና ሀይልን በማድከም ወንጀል ላይ ከመውደቅ የሚከላከል ነው። ሁለተኛው: ሰደቃ (ግዴታ ያልሆነ ምፅዋት) መስጠት ነው። ይህም ወንጀል ከተሰራ በኋላ ወንጀልን ታጠፋለች፣ ታስወግዳታለች፣ ፋናዋንም ታብሳታለች። ሶስተኛው: በሌሊቱ የመጨረሻ ሲሶ የተሀጁድ ሶላት መስገድ ነው። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) {ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ} በሶላት፣ በዚክር፣ በመቅራትና በዱዓ {ጌታቸውን ይጠሩታል።} {ለመፍራትና ለመከጀል ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለግሳሉ። ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።} ማለትም የትንሳኤ ቀን በጀነት ውስጥ በሚያገኙት ፀጋ አይኖቻቸው በርሱ የምትረጋበትን ነፍሳቸው አታውቅም። {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት።} ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: የሃይማኖቱ መሰረት የሆነውን አልነግርህምን? መሰረቱ በርሱ ላይ የሚደገፍበት ምሰሶውንስ አልነግርህምን? ሻኛውንስ አልነግርህምን? ሙዓዝም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "እንዴታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አለ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: የነገሮች ራስ (ዋና) እስልምና ነው። እርሱም ሁለቱ የምስክር ቃላቶች ናቸው። የሃይማኖቱ መሰረት ከሰውዬው ጋር የሚቆይለት በሁለቱ ቃላት ነው። ምሰሶው: ሶላት ነው። ቤት ያለምሰሶ እንደማይኖር ሁሉ ያለ ሶላትም እስልምና የለም። የሰገደ ሰው ሃይማኖቱ ይጠነክራልም ከፍ ይላልም። ሻኛውና ከፍታው ደሞ በጂሃድና የአላህን ቃል ከፍ ለማድረግ የእስልምና ጠላቶችን ለመዋጋት አቅምን በመለገስ ነው። ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: ቀደም ብዬ የነገርኩህን ነገር የሚያስረውና የሚጠብቀውን ልንገርህን? ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምላሳቸውን ያዙና "ይህንን ቆጥብ። የማይመለከትህን አትናገር።" አሉት። ሙዓዝም: "ጌታችን በምንናገረው ሁሉ ይቀጣናል? ይተሳሰበናል? ይይዘናልን?" አላቸው። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እናትህ ትጣህ" አሉት። በዚህም እርሱን መርገም ፈልገው ሳይሆን ነገር ግን ዐረቦች ሊታወቅና ሊገነዘቡት የሚገባን ነገር ለማስገንዘብ የሚናገሩት ንግግር ነው። ቀጥለው "እንደ ክህደት፣ ዘለፋ፣ ስድብ፣ ሀሜት፣ ነገር ማሳበቅ፣ ቅጥፈትና በመሳሰሉት ምላሳቸው ባጨደችው ክፋት ካልሆነ በቀር ሰዎችን እሳት ውስጥ በፊታቸው የሚጥላቸውና የሚደፋቸው (ሌላ ነገር) አለ እንዴ?" አሉት።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ መልካም (ጥሩ) ነውና ከመልካም (ከጥሩ) በቀር አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል። አላህ እንዲህ ብሏል: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስሩ። እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝ።} [አልሙእሚኑን:51] እንዲህም ብሏል: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮችን ብሉ።} [አልበቀራህ: 172]" ቀጥለውም ጉዞ የሚያረዝም፣ ጨብራራ፣ ፊቱንና ልብሱን አቧራ ያለበሰው አንድ ሰውዬ አወሱ። እጁን ወደ ሰማይ እየዘረጋ: "ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! እያለ ይለምናል። ምግቡ ሐራም ነው። መጠጡ ሐራም ነው። ልብሱ ሐራም ነው። በሐራም ነው የተገነባው። እንዴት ለርሱ ዱዓው ተቀባይነት ይኖረዋል?" አሉ።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ መልካም፣ ከጉድለትና ነውር የጠራና የፀዳ፣ በምሉዕነት የሚገለፅ መሆኑን ተናገሩ፤ ከተግባርም፣ ከንግግርና ከእምነትም መልካም የሆነውን እንጂ እንደማይቀበል ተናገሩ። እርሱም ለአላህ ጥርት ተደርጎ የተሰራና የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ የተከተለ ስራ ነው። በዚህ ካልሆነ በቀርም ወደ አላህ መቃረብ አይገባም። ለአንድ አማኝ ስራው መልካም ከሚሆንበት ትላልቅ ነገሮች መካከል ምግቡ መልካም መሆኑ ነው። ይህም የተፈቀደውን መመገቡ ነው። በዚህም ስራው ይፀዳል። ስለዚህም የተፈቀደን በመብላትና መልካም በመስራት አላህ መልክተኞችን እንዳዘዘው ሁሉ አማኞችንም አዘዘ። አላህ እንዲህ አለ: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስሩ። እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝ።} እንዲህም አለ: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮችን ብሉ።} ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምንም ያህል ተቀባይነትን የሚያስገኙ ግልፅ ሰበቦችን ቢፈፅም ስራን የሚያበላሽና ተቀባይነቱን የሚያሳጣ ከሆነው ሐራም ምግብ ከመብላት አስጠነቀቁ። ለዱዓ ተቀባይነትን ያስገኛሉ ከተባሉት ግልፅ ሰበቦች መካከልም: የመጀመሪያ: እንደ ሐጅ፣ ጂሃድ፣ ዝምድናን መቀጠልና ከዚህም ውጪ ላሉ ነገሮች ለአምልኳዊ አላማዎች ጉዞን ማርዘም ነው። ሁለተኛው: ባለማበጠር ምክንያት የፀጉሩ መበታተንና በአፈር (በአቧራ) ምክንያት የልብሱ ቀለምና የሰውነት መልኩ መለወጡ ነው። ይህም አስገዳጅ ችግር የገጠመው መሆኑ ነው። ሶስተኛው: ወደ ሰማይ ዱዓ በማድረግ እጁን ከፍ ያደርጋል። አራተኛው: ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! እያለ ወደ አላህ በስሞቹ ይቃረባል፣ በዚህም ችክ ይላል። ከነዚህ ለዱዓ ተቀባይነትን ከሚያስገኙ ምክንያቶች ጋር ሆኖም ግን ዱዓው አልተሰማም። ይህም ምግቡ፣ መጠጡና ልብሱ ሐራም ስለሆነና በሐራም ስለተገነባ ነው። ባህሪው ይህ የሆነ ሰው ተቀባይነት ማግኘቱም ሩቅ ነው። አላህስ እንዴት ዱዓውን ይቀበለዋል?
ከሚቅዳድ ቢን ዐምር አልኪንዲይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ለአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አላቸው: «ከከሀዲዎች መካከል ከአንዱ ጋር ብንገናኝና ብንጋደል አንድ እጄንም በሰይፉ መቶ ቢቆርጣት ከዚያም ከኔ ለማምለጥ ወደ ዛፍ ተጠግቶ ለአላህ ብዬ እስልምናን ተቀብያለሁ ቢል የአላህ መልክተኛ ሆይ! ንገሩኝ እስኪ ይህን ከተናገረ በኋላ ልግደለውን? የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እንዳትገድለው።" አሉ። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ እጄን‘ኮ ቆርጧል። ከዚያም እጄን ከቆረጣት በኋላ ነው ይህቺን የተናገራት!" አለ። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እንዳትገድለው! ከገደልከው እርሱ ከመግደልህ በፊት የነበርክበት ደረጃ ላይ ይሆንና አንተ ደሞ የተናገረውን ንግግር ከመናገሩ በፊት በነበረው ደረጃ ላይ ትሆናለህ።" አሉ።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ሚቅዳድ ቢን አስወድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና -ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጦርነት ላይ ከአንድ ከሀዲ ሰው ጋር ቢገናኝና በሰይፍ ብቻ ለብቻ ቢጋጠሙ ከሀዲውም አንድ እጁን በሰይፍ አግኝቶ ከቆረጠ በኃላ ከርሱ ሸሽቶ በዛፍ ቢመሸግና "ላኢላሃ ኢለሏህ" ቢል እጄን ከቆረጠ በኋላ እርሱን መግደል ይፈቀድልኛልን? በማለት ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዳትገድለው! አሉት። እርሱም: የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሱ’ኮ አንድ እጄን ቆርጧል። ይህን ከማድረጉም ጋር አልገድለውምን? አላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: እንዳትገድለው! እርሱ ደሙን ማፍሰስ ከተከለከሉት ሆኗል። ከሰለመ በኋላ ከገደልከው እርሱ በእስልምናው ደሙ የተጠበቀ ስለሆነ ባንተ ደረጃ ይሆንና አንተ ደሞ እርሱን በመግደልህ በቂሷስ ህግ መሰረት ደምህ መፍሰሱ የተፈቀደ ስለምትሆን በርሱ ደረጃ ላይ ትሆናለህ! አሉት።
ከአቡ በርዛህ አልአስለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"
ቲርሚዚ ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን ከሒሳብ መተሳሰቢያ ስፍራ አንድም ሰው ስለተወሰኑ ጉዳዮች ሳይጠየቅ ወደ ጀነት ወይም ወደ እሳት እንደማያልፍ ተናገሩ። የመጀመሪያው: ህይወቱን በምን እንዳጠፋውና እንዳሳለፈው? ሁለተኛው: ዕውቀቱን ለአላህ ብሎ ነው የፈለገው? በእውቀቱ ሰርቶበታልን? ማወቅ ለሚገባውስ አስተላልፎታልን? ሶስተኛው: ገንዘቡን ከየት ነው ያገኘው? ከሐላል ነው ወይስ ከሐራም? ለምንስ አዋለው? አላህን በሚያስደስት ነገር ላይ አዋለው? ወይስ በሚያስቆጣው ነገር ላይ? አራተኛው: ስለ አካሉ፣ ሀይሉ፣ ጤንነቱ፣ ወጣትነቱ ነው። ምን ላይ ተጠቅሞ እንዳሳለፈው?
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የኸይበር ቀን እንዲህ አሉ: «"አላህና መልክተኛውን ለሚወድ፣ አላህም በእጁ ድልን የሚያጎናፅፈው ለሆነ አንድ ሰው ይህንን ባንዲራ እሰጣለሁኝ።" ዑመር ቢን አልኸጧብ እንዲህ አሉ: "ከዚያ ቀን ውጭ ሹመትን ወድጄ አላውቅም። ለርሷ እንድጠራ በመከጀልም ተንጠራራሁኝ።" የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብን ጠርተው ባንዲራውን ሰጡት። እንዲህም አሉት "አላህ ባንተ ላይ ድልን እስኪያጎናፅፍ ሳትዞር ተጓዝ።" ዐሊይ ጥቂት ተጓዘ ከዚያም ሳይዞር ቆም አለና ጮኽ ብሎ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎቹን በምን ላይ ነው የምዋጋው?" አላቸው። እርሳቸውም "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ ተዋጋቸው። ይህንን ከፈፀሙ ደማቸውንና ገንዘባቸውን በሐቁ ካልሆነ በቀር ከአንተ ተከላክለዋል። ሒሳባቸው ግን አላህ ዘንድ ነው።" አሉ።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነገ በመዲና አቅራቢያ በምትገኘው የኸይበር ከተማ አይሁዶች ላይ ሙስሊሞች ድልን እንደሚያገኙ ለሶሐቦች ተናገሩ። ይህም ባንዲራውን በሚሰጡት ሰው እጅ ነው። ባንዲራ ማለት ለመታወቂያነት ሰራዊቱ የሚይዘው ምልክት ነው። ይህ ሰው ከባህሪዎቹ መካከል አላህና መልክተኛውን ይወዳል፤ አላህና መልክተኛውም ይወዱታል። ዑመር ቢን አልኸጣብም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከዛ ቀን በቀር ሹመትን እንዳልወደዱና አላማ አድርገው እንዳልያዙ አወሱ። ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህና መልክተኛውን ይወዳል ብለው ያወሱትን መገለጫ ለማግኘት በመከጀል ነው። ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አይተውት እንዲጠሩት ይህንንም ባንዲራ ለመያዝ በመጓጓትና በመከጀል ተንጠራሩ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጠርተው ባንዲራውን ሰጡት። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰራዊቱን ይዞ እንዲንቀሳቀስ፤ ጠላቶቹን ከተገናኘ በኋላም ምሽጎቹን በድልና በማሸነፍ አላህ እስኪከፍትለት ድረስ በእረፍትም ይሁን ወይ በማቆም አለበለዚያም በስምምነት ምክንያት ጦርነቱን እንዳያቆም አዘዙት። ዐሊይም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - ተጓዙ ከዚያም የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትእዛዝ ላለመፃረር ሳይዞሩ ቆም ብለው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎቹን በምን ላይ ነው የምዋጋቸው?" አሉ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ ተዋጋቸው። ይህን ተቀብለው ወደ እስልምና ከገቡ ደምና ገንዘባቸውን ከአንተ ተከላክለዋል። በአንተም ላይ እርም ተደርጓል። በሐቁ ካልሆነ በቀር ማለትም በእስልምና ህግጋት መሰረት በርሱ ሊገደሉበት የሚገባቸውን ወንጀል ወይም ግድያ እስካልፈፀሙ ድረስ እንዳትገድላቸው ማለት ነው። ሒሳባቸው ታዲያ አላህ ዘንድ ነው።
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደድ፣ ከማዘን፣ ከመርዳት፣ ከማገዝና እነርሱ ላይ በሚደርስ ጉዳት አብሮ ከመጎዳት አንፃር ሙስሊሞች ከፊሉ ለከፊሉ ሊኖረው የሚገባውን ሁኔታ ልክ እንደ አንድ ሰውነት ምሳሌ ሊሆን እንደሚገባው ግዴታነቱን ገለፁ። አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው አካል በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት አብሮት ይሰቃያል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ጉንጩን የመታ፣ አንገትያውን የቀደደ፣ በድንቁርና ጥሪ የተጣራ ከኛ አይደለም።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአንዳንድ የድንቁርና ዘመን ሰዎች ተግባር አስጠነቀቁም ከለከሉም። እንዲህም አሉ: እነዚህ ከኛ አይደሉም: የመጀመሪያው: ጉንጩን የመታ ነው። ጉንጭን የለዩት በአብዛኛው የሚፈፀመው እርሱ ስለሆነ ነው እንጂ የተቀሩትን የፊት ክፍልን መምታትም ክልከላው ውስጥ ይካተታል። ሁለተኛው: ልብስ ላይ ጭንቅላት እንዲገባበት ተብሎ የሚከፈተውን (አንገትያ) ከትእግስት ማጣት ብዛት መቅደድ ነው። ሶስተኛው: የድንቁርና ዘመን ጥሪዎችን መጣራት ነው። ለምሳሌ ያህል፦ ወዮልኝ፣ ወይኔ በጠፋው ማለት፣ ሙሾ ማውረድ፣ እየገጠሙ ማለቃቀስና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመና ቢደርሱና ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን ሊሞላ በቀረበ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣ ከዚያም በኔ አንድንም ሳታጋራብኝ ብትገናኘኝ እኔም ምድርን ሊሞላ በቀረበ ምህረት ወዳንተ እመጣለሁ።›"»
ቲርሚዚ ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሐዲሠል ቁድስ ውስጥ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: የአደም ልጅ ሆይ! እኔን በመለመን፣ እዝነቴን በመከጀልና ተስፋ ባለመቁረጥ ላይ እስከዘወተርክ ድረስ ይህ ወንጀልህና ሀጢዐትህ ከትላልቅ ወንጀሎች ቢሆንም እንኳ እሸሽገዋለሁ፣ ምንም ሳይመስለኝም አብሰዋለሁ። የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀልህ በሰማይና በምድር መካከል ያለውን በሚሞላና ምድርንም ከጫፍ እስከጫፍ በሚደርስና ጎኖቿን በሚያጠቃልል መልኩ ቢበዛ ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ ብዛቱ ምንም ሳይመስለኝ ሁሉንም ላንተ አብሰዋለሁም እምርሃለሁኝም። የአደም ልጅ ሆይ! አንተ ከሞት በኋላ ወደኔ ምድርን በሚሞላ ወንጀሎችና ሀጢዐቶች ብትመጣ በብቸኝነቴ አምልከኸኝ በኔ አንድንም ሳታጋራ ከሆነ የሞትከው እነዚህን ወንጀሎችህንና ሀጢዐቶችህን ምድርን በሚሞላ ምህረት እገናኛቸዋለሁ። እኔ ምህረተ ሰፊ ነኝና። ከሺርክ በስተቀርም ሁሉንም ወንጀሎችህን እምራለሁ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው። በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ! በአላህም ታገዝ! አትስነፍ! አንዳች ነገር ሲያገኝህም ‹እንዲህ አድርጌ በነበር እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር።› አትበል። ይልቁንም ‹ይህ የአላህ ውሳኔ ነው። የሻውንም ፈፀመ።› በል። (እንዲህ ቢሆን ኖሮ) ማለት የሰይጣንን ስራ ትከፍታለችና።'"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙእሚን ሁሉ ነገሩ መልካም እንደሆነ፤ ነገር ግን በኢማኑ፣ በቆራጥነቱ፣ በገንዘቡም በሌላም የኃይል ጎን ጠንካራ የሆነው ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን የበለጠ አላህ ዘንድ ምርጥና ተወዳጅ መሆኑን ገለፁ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አማኝ ለሆነ ሰው ጥራት በተገባውና ከፍ ባለው አላህ ላይ ከመመካትና ከመታገዝ ጋር ለዱንያዊም ይሁን ለአኺራዊ ጉዳዮቹ የሚጠቅመውን ሰበቦች መያዝ እንደሚገባው መከሩ። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሁለቱ ዓለም የሚጠቅሙ ነገሮችን ከመተግበር መዳከም፣ መታከትንና መሳነፍን ከለከሉ። አማኝ የሆነ ሰው በአላህ በመታገዝ በአንድ ስራ ላይ ከታገለ፣ ሰበቦችን ከያዘና ከአላህ መልካሙን ከፈለገ በኋላ ሁሉን ነገሩ ወደ አላህ ማስጠጋትና የአላህ ምርጫ የተሻለ መሆኑን ማወቅ እንጂ ሌላ ጣጣ ውስጥ መግባት የለበትም። ከዚህም በኋላ አንድ ችግር ቢያገኘው እንዲህ ማለት የለበትም: "እንዲህ ባደርግ ኖሮ እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር።" ""እንዲህ ባደርግ ኖሮ" ማለት የአላህን ውሳኔ በመቃወም፣ ባለፈ ነገር በመቆጨት፣ የሰይጣንን ስራ ትከፍታለች። ነገር ግን በመቀበልና በመውደድ "ይህ የአላህ ውሳኔ ነው። አላህም የፈለገውን ፈፀመ።" ይበል። የተከሰተው ነገር አላህ በፈለገው መሰረት ነው። እርሱ የፈለገውን ነገር ፈፃሚ ነው፤ የርሱን ውሳኔ መላሽ የለም፤ ፍርዱንም የሚያቅብ የለም።