





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል "አላህ እንዲህ አለ: እኔ ባሪያዬ ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባስታወሰኝም ጊዜ እኔ ከርሱ ጋር ነኝ። ለብቻው ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ፤ በህብረት ካወሳኝ ደሞ ከርሱ የተሻለ በሆኑ ህብረቶች ዘንድ አወሳዋለሁ። አንድ ስንዝር ወደኔ ከቀረበ አንድ ክንድ ወደርሱ እቀርባለሁ። አንድ ክንድ ወደኔ ከቀረበ እጅ ሙሉ ወደርሱ እቀርባለሁ። እየተራመደ ወደኔ ከመጣ በሶምሶማ ወደርሱ እመጣለሁ።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ እንዲህ ማለቱን ተናገሩ: እኔ ባሪያዬ እኔን ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባሪያዬ ስለኔ ባለው እሳቤ አስተናግደዋለሁ። ይህም ተስፋ በማድረግ፣ ይቅርታዬን በመመኘት ነው። መልካምም ሆነ ከዛ ውጪ ከኔ ተስፋ ያደረገውን ከኔ ያገኛል። እኔን ካወሳኝ በእዝነቴ፣ በመግጠም፣ በመምራት፣ በመጠበቅና በማገዝ ከርሱ ጋር እሆናለሁ። ለብቻው ተገልሎ በ"ተስቢሕ"፣ በ"ተህሊል" ወይም በሌሎች ዚክሮች ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ። በህብረት ካወሳኝ እርሱ እኔን ካወሳበት ህብረት በተሻለና በበዛ ምርጥ ህብረት እርሱን አወሳዋለሁ። ወደ አላህ የስንዝር ያህል ለተቃረበ ሰው አላህም ጨምሮ የክንድ ያህል ወደርሱ ይቀርባል። ክንድ ያህል ወደርሱ ከተቃረበ አላህም ሁለት ክንድ የሚያህል ወደርሱ ይቀርባል። እየተራመደ ወደ አላህ ከመጣ አላህም ወደርሱ በሶምሶማ ይመጣል። አንድ ባሪያ አላህን በመታዘዝና ወደርሱ በመዞር የተቃረበ ጊዜ በሰራው ስራ ትይዩ ለመመንዳት ጌታም ወደርሱ መቃረብን ይጨምርለታል። አንድ አማኝ ለጌታው ያለው ባርነት በተሟላ ቁጥር አላህም ወደርሱ ይቀርባል። የአላህ ስጦታና ምንዳ ከባሪያው ስራና ጥንካሬ የበለጠ ነው። ዋናው ፍሬ ሀሳብ በቁጥርም ሆነ ሁኔታ የአላህ ምንዳ ከስራ ታመዝናለች የሚለው ነው። አማኝ የሆነ ሰው በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ያሳምራል። አላህን እስኪገናኝ ድረስም ይጨምራልም ይፈጥናልም።
ከጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ፀጉሩ የተበታተነ የነጅድ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣ፤ ወደ አላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስኪቀርቡ ድረስ ከፍ ያለ ድምፁን እንሰማ ነበር ነገር ግን የሚናገረውን ልንረዳው አልቻልንም፤ ለካ ስለ እስልምና እየጠየቀ ኖሯል። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲመልሱለት "በቀንና በምሽት የሚሰገድ አምስት ሶላቶች ነው።" አሉት። እርሱም "ከነዚህ ሶላቶች በቀር ሌላ ሶላት አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፍቃደኝነት (የምተሰግደው ሶላት) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም። እንዲሁም የረመዳንን ወር መጾም።" አሉት። እርሱም "ከዚህ ጾም በቀር ሌላ ጾም አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፍቃደኝነት (የምትጾመው ጾም) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም።" አሉት። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘካንም አወሱለት። እርሱም "ከዚህ ውጪ ሌላ የምፅዋት ግዴታ አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፈቃደኝነት (የምትመፀውተው) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም።" አሉት። ሰውዬውም "በአላህ እምላለሁ! ከዚህ አልጨምርምም አልቀንስምም።" እያለ ዞሮ ሄደ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እውነቱን ከተናገረ ስኬታማ ሆነ!" አሉ።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አንድ ፀጉሩ የተበታተነ፣ ድምፁ ከፍ ያለ፣ የሚናገረው የማይገባ የነጅድ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣ። ወደነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀረበና ስለ እስልምና ግዴታዎችም ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶላት ጀመሩና አላህ በሁሉም ቀንና ምሽቶች አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገበት ነገሩት። እርሱም: ከነዚህ አምስት ሶላቶች በቀር ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ? አላቸው። እርሳቸውም: ሱና ሶላቶችን በፈቃደኝነት ልትሰግድ ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም አሉት። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው እንዲህ አሉት: በአንተ ላይ አላህ ግዴታ ካደረገብህ ነገሮች መካከል የረመዳንን ወር መጾም አንዱ ነው። ሰውዬውም "ከረመዳን ጾም ውጪ ሌላ ጾም መጾም ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ?" አላቸው። እርሳቸውም: በፈቃደኝነት ካልጾምክ በቀር የለብህም አሉት። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘካን አወሱለት። ሰውዬውም: የግዴታ ዘካዬን ካወጣሁ በኋላ ሌላ ምፅዋት ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ? አላቸው። እርሳቸውም: በፈቃደኝነት ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም አሉት። ሰውዬው እነዚህን ግዴታዎች ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰማ በኋላ ከእነሱ ምንም ሳይጨምርና ሳይቀንስ ዘውትሮ እንደሚተገብር በአላህ ምሎ እየተናገረ ዞሮ ሄደ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ይስፈንና ይህን አስከትለው ሰውዬው የማለበትን ነገር የእውነት ከፈፀመ ከሚድኑት ሰዎች ይሆናል አሉ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን ኣደም ተፈጠረ፣ በዚሁ ቀን ጀነት ገባ፣ በዚሁ ቀን ከርሷ ወጣ፣ ሰአቲቱም በጁመዓ ቀን ካልሆነ በቀር አትከሰትም።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓ ቀን እንደሆነ ተናገሩ። የጁሙዓን ቀን ልዩ ከሚያደርገው ነገሮች መካከል: አላህ አደምን (ዐለይሂ ሰላም) የፈጠረው፣ ጀነት ውስጥ ያስገባው፣ ከጀነት አስወጥቶ ወደ ምድር ያወረደው በዚሁ ቀን ነው። ሰአቲቱም በጁሙዓ ቀን ካልሆነ በቀር አትከሰትም።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ " አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር በዱንያ አይሸፍንም፤ የትንሳኤ ቀን አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም የሙስሊም ወንድሙን ነውር የሚሸፍን ከሆነ አላህ የትንሳኤ ቀን የርሱን ጉዳይ የሚሸፍንለት መሆኑን ገለፁ። የስራ ክፍያ እንደስራው አይነት ነው። አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ነውሩንና ወንጀሉን ከተቀሰቀሱ ፍጡራን በመሸሸግ ነው። በዛ ወንጀል መተሳሰብና ለርሱ ማውሳቱን በመተውም ሊሆን ይችላል።
ከአቡ ሙስሊም አልኸውላኒ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ "ተወዳጁና ታማኙ ሰው ይህንን ሐዲሥ ነገረኝ። እርሱ እኔ ዘንድ ተወዳጅነትም ታማኝነትም አለው። ይሀውም ዐውፍ ቢን ማሊክ አልአሽጀዒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: 'የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ ዘጠኝ ወይም ስምንት ወይም ሰባት ሆነን ሳለ እንዲህ አሉን ‹ለአላህ መልክተኛ ቃል አትጋቡምን?› ቃልኪዳን ከተጋባናቸው ቅርብ ጊዜ ነበርንና ‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርግጥ ቃልኪዳን ተጋብተኖታል'ኮ› አልናቸው። ቀጥለውም ‹ለአላህ መልክተኛ ቃል አትጋቡምን?› አሉ። እኛም ‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርግጥ ቃልኪዳን ተጋብተኖታል'ኮ› አልናቸው። ቀጥለውም ‹ለአላህ መልክተኛ ቃል አትጋቡምን?› አሉ። የዛኔ እጃችንን (ቃልኪዳን ለመጋባት) ዘርግተን ‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርግጥ ቃልኪዳን ተጋብተኖታል። በምን ጉዳይ ላይ ነው ቃልኪዳን የምንጋባዎት?› አልናቸው። እርሳቸውም ‹አላህን በርሱ አንዳችም ሳታጋሩ በመገዛት፣ በአምስቱ ሶላቶች ላይ፣ በታዛዥነት፣ (ዝግ ባለ ድምፅ የተወሰኑ ቃላቶችን ተናገሩ።) ሰዎችን አንዳችም ነገር ባለመጠየቅ።› አሉን።' በርግጥም ከነዚህ (ቃልኪዳን ከተጋቡት ውስጥ) የተወሰኑትን የአንዳቸው አለንጋ ወድቆ አንድንም ሰው እንዲያቀብለው የማይጠይቅ ሆኖ ተመልክቻለሁ።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከተወሰኑ ሶሐቦች የሆኑ ጉዳዮችን አጥብቆ ለመያዝ ቃልኪዳን እንዲጋቡዋቸው ሶስት ጊዜ ፈለጉ። የመጀመሪያው: አላህን ትእዛዙን በመተግበር ክልከላውን በመራቅ በብቸኝነት ማምለክና በርሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው። ሁለተኛው: አምስቱን ግዴታ ሶላቶች በቀንና በምሽት ቀጥ አድርጎ መስገድ ነው። ሶስተኛው: የሙስሊሞችን ጉዳይ እንዲመራ ለተሾመ ሰው በመልካም ጉዳዮች ሰምቶ መታዘዝ ነው። አራተኛው: ሁሉንም ጉዳያቸውን ወደ አላህ በማስጠጋት ሰዎችን አንዳችም ነገር አለመጠየቅ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ሲናገሩ ድምፃቸውን ዝግ አደረጉ። ሐዲሡን ያስተላለፈው፦ "ከነዚህ ሶሐቦች የተወሰኑትን የአንዳቸው አለንጋ ሲወድቅ እንኳ ወርዶ በራሱ ያነሳዋል እንጂ አንድም ሰው አለንጋውን እንዲያቀብለው የማይጠይቅ ሆነው ተመልክቻቸዋለሁ።" ብሎ እስኪገልፃቸው ድረስ ሶሐቦቹ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የተጋቡትን ቃልኪዳን ተግባራዊ አድርገውታል።
ከበራእ ቢን ዓዚብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።" ይህም አላህ እንዲህ እንዳለው ነው: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አማኝ ቀብር ውስጥ ይጠየቃል። ለዚህ ስራ የተወከሉ ሁለት መላእክት ይጠይቁታል። እነሱም በበርካታ ሐዲሦች ስማቸው እንደተጠቀሰው ነኪርና ሙንከር ናቸው። ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ነው አላህ የተረጋገጠው ቃል ብሎ የተናገረበት አሉ: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ናቸው ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስኪሰግዱና ዘካን እስኪሰጡ ድረስ ሰዎችን እንድጋደል ታዝዣለሁ። ይህንን ከፈፀሙ በኢስላም ሐቅ ካልሆነ በቀር ደማቸውና ገንዘባቸውን ከኔ ጠብቀዋል። ሒሳባቸውም አላህ ዘንድ ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አጋርያን ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ብቸኛና አጋር እንደሌለው እስኪመሰክሩ፤ በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልክተኝነት እስኪመሰክሩና ይህ የምስክር ቃል በሚያስፈርደው ነገሮች እስከሚተገብሩ ለምሳሌ በቀንና ምሽት ውስጥ አምስት ሶላቶችን መስገድ ላይ በመጠባበቅ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ ለሚገባው እስኪሰጡ ድረስ አላህ አጋርያንን እንዲጋደሉ እንዳዘዛቸው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ። እነዚህን ጉዳዮች የሰሩ ጊዜ ኢስላም ደማቸውንና ገንዘባቸውን ይጠብቅላቸዋል። በኢስላም ህግጋት መሰረት ለግድያ የሚያበቃቸውን ወንጀል ወይም ጉዳት እስካልፈፀሙ ድረስም እነርሱን መግደል አይፈቀድም። ከዚያም እነርሱን መተሳሰቡን የትንሳኤ ቀን ውስጣቸውን በሚያውቀው አላህ ቁጥጥር ይሆናል።
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "አላህ ለኔ ከኡመቴ ላይ በመሳሳት፣ በመርሳትና በመገደድ ለሚያደርጉት ነገር ይቅር ብሏቸዋል።"»
رواه ابن ماجه والبيهقي وغيرهماነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ ለኡመታቸው በሶስት ሁኔታዎች ላይ እያሉ የሰሩትን ወንጀል ይቅር እንዳለ ተናገሩ:- የመጀመሪያው: በስህተት: ማለትም ሆነ ብለው ሳይሆን የሰሩት ወንጀል ማለት ነው። ይህም ማለት አንድ ሙስሊም በድርጊቱ አንዳችን ነገር ማሰቡና ድርጊቱ ግን ካሰበው ውጪ ሆኖ መገኘቱ ነው። ሁለተኛው: በመርሳት: ይህም ማለት አንድ ሙስሊም አንድን ነገር ለመስራት ያስባል። ነገር ግን ድርጊቱን ለመስራት ባሰበበት ወቅት ይረሳዋል። በዚህም ወንጀል አይኖርበትም። ሶስተኛው: በመገደድ ነው። አንድ ባሪያ መስራት ሳይፈልግና አስገዳጁንም አካል መከላከል በማይችልበት ሁኔታ ላይ ሆኖ ተገዶ አንድን ድርጊት ሊሰራ ይችላል። በዚህ ጊዜ በርሱ ላይ ወንጀል ወይም ጣጣ አይኖርበትም። የሐዲሡ ሃሳብ ግን በባሪያና በጌታው መካከል የተከለከለን በመስራት ላይ መርሳትን የሚመለከት ነው። ትእዛዝን ረስቶ ቢተው ግን ትእዛዙ አይነሳለትም። እነዚህን ነገሮች ተከትሎ የተከሰተ ወሰን አላፊነት ካለ የፍጡርም ሐቅ አይነሳለትም። በስህተት የገደለ ሰው ለምሳሌ በርሱ ላይ ጉማ ይኖርበታል። ወይም በስህተት መኪና ቢያጠፋ በርሱ ላይ መኪናውን መክፈል አለበት።
ከሶፍዋን ቢን ሙሕሪዝ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አንድ ሰውዬ ለኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አለ: "የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለ መመሳጠር ሲናገሩ የሰማሀው ነገር አለን?" እርሱም አለ: "እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹አንድ አማኝ የትንሳኤ ቀን ወደ ጌታው ይቀርባል። በርሱ ላይ መሸፈኛውን አኑሮበት ወንጀሎቹን እንዲያምን ያደርገዋል። 'አወቅከውን?' ይለዋል። እርሱም 'ጌታዬ አውቄዋለሁ።' ይላል። አላህም 'እኔ በዱንያ ውስጥ ባንተ ላይ ሸፍኛት ነበር። ዛሬ ደግሞ ላንተ እምርሃለሁ።' ይለዋል። የመልካም ስራ መጽሐፉም ይሰጠዋል። ከሀዲዎችና ሙናፊቆች ግን በፍጡራን መካከል ይጠሩና 'እነዚህ በአላህ ላይ ያስተባበሉ ናቸው' ይባላሉ።›"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ አንድ አማኝ ባሪያውን የትንሳኤ ቀን እንደሚመሳጠረው እንዲህ በማለት ተናገሩ: የትንሳኤ ቀን አማኝ የሆነ ሰው ወደ ጌታው ይቀርባል። ከርሱ ውጪ አንድም ሰው ምስጢሩን እንዳያውቅበትም ከቆሙ ሰዎች ይከልለዋል። እንዲህም ይለዋል: "እንዲህ እንዲህ ... ወንጀልህን አወቅከው?" እያለ በባሪያውና በጌታው መካከል የሰራውን ወንጀሎች እንዲያረጋግጥ ያደርገዋል። እርሱም "አዎ ጌታዬ" ይላል። አማኙ የደነገጠና የፈራ ጊዜም አላህ ሱብሓነሁ እንዲህ ይለዋል: "ምድር ላይ ላንተ ሸፍኜልሃለሁ። ዛሬ ደግሞ ላንተ እምርሃለሁ።" የመልካም ስራ መጽሐፉም ይሰጠዋል። ከሀዲና ሙናፊቅ ግን በፍጡራን መካከል እየተጠሩ እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹ ናቸው። አዋጅ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን ይባላሉ።