





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው። ከአንዳች ነገር የከለከልኳችሁ ጊዜ ራቁት፤ በአንድ ትእዛዝ ያዘዝኳችሁ ጊዜ ደሞ የቻላችሁትን ያህል ከርሱ ፈፅሙ!"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሸሪዓ ድንጋጌዎች ለሶስት እንደሚከፈሉ ገለፁ። እነሱም: ዝም የተባለ፣ ክልከላዎችና ትእዛዛት ናቸው። የመጀመሪያው: አላህና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለርሱ ዝም ያሉት ነው። ፍርድ ከሌለው የነገሮች መሰረቱ ግዴታ አለመሆኑ ነው። በርሳቸው ዘመን ስለአንዳች ስላልተከሰተ ነገር መጠየቅን መተው ግዴታ ነበር። ይህም በርሳቸው ላይ ግዴታ የሚያደርግ ወይም ክልክል የሚያደርግ መመርያ እንዳይወርድ ነው። አላህ የተዋት ለባሮቹ በማዘኑ ነውና። እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሞቱ በኋላ ግን ጥያቄው ፈታዋ በመጠየቅ መልኩ ወይም በሃይማኖቱ ጉዳይ የሚያስፈልገውን በመማር መልኩ የቀረበ ከሆነ ይህ የተፈቀደ ብቻ ሳይሆን የታዘዘበትም ጭምር ነው። ጥያቄን የጠየቀው ተጨንቆ ፈጥሮና በግትርነት ከሆነ ግን እዚህ ሐዲሥ ውስጥ መጠየቅን በመተው የተፈለገው ይህ አይነቱን ነው። ይህም በኒ ኢስራኤሎች ላይ የተከሰተው አምሳያ ወደመከሰት ስለሚያመራ ነው። ይህም ላም እንዲያርዱ በታዘዙ ወቅት ማንኛውንም የላም አይነት ቢያርዱ ትእዛዙን እንደፈፀሙ ይቆጠርላቸው ነበር። ነገር ግን እነሱ በመጠየቅ ሲያጠብቁት ትእዛዙም ጠበቀባቸው። ሁለተኛው: ክልከላዎች ናቸው: ይህም መተዉ የሚያስመነዳ መተግበሩ የሚያስቀጣ ነው። ይህንንም ሙሉ ለሙሉ መራቅ ግዴታ ነው። ሶስተኛው: ትእዛዝ ነው። እርሱም መስራቱ የሚያስመነዳ መተዉ የሚያስቀጣ ነው። በአቅም ልክ መተግበሩም ግዴታ ነው።
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ አላህ እንዲህ አለ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከዚያም ይህንን አብራርቷል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል ። እሱ (ለመስራት) አስቧት ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም አልፎ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎች ይጽፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን እንደወሰነ ከዚያም ለሚፅፉት ሁለት መላእክቶች እንዴት እንደሚፅፉት እንዳብራራ ገለፁ። መልካምን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ሰው ባይሰራትም እንኳ ለሱ አንድ ምንዳ ትፃፍለታለች። ከሰራት ደግሞ በስራዋ አምሳያ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ከዚያም አልፎ እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ ትባዛለች። ይህ የምንዳ ጭማሪው ቀልቡ ውስጥ ባለው ኢኽላስ፣ በጥቅሙ ወደ ሌሎች ተሻጋሪነትና በመሳሰሉት ልክ ተንተርሶ ነው ። ኃጢዐትን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ከዚያም ለአላህ ብሎ ሳይሰራት የተዋት ሰው ለሱ አንድ ምንዳ ይጻፍለታል። ወደዛች ኃጢዐት የሚያዳርሱ መንስኤዎችን ካለመፈፀም ጋር በሌላ ነገር በመጠመዱ ሳቢያ ከተዋት ምንም ነገር አይፃፍለትም። ኃጢዐቱን መስራት ስለተሳነው ከተወ ደግሞ በሱ ላይ ያለመው ትፃፍበታለች። ከሰራት ደግሞ አንዲት ሀጢዐት ትፃፍበታለች።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ወደ ሰዎች ቅርፅና ሰውነት ያምራል ወይስ አስቀያሚ ነው? ትልቅ ነው ወይስ ትንሽ? ጤነኛ ነው ወይስ በሽተኛ? በማለት እንደማይመለከት ገለፁ። ወደ ገንዘቦቻቸውም ብዙ ነው ወይስ ትንሽ? በማለት አይመለከትም። አላህ ባሮቹን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ባላቸው መበላለጥ ተንተርሶ አይቀጣቸውምም አይተሳሰባቸውምም። ነገር ግን በቀልቦቻቸው ውስጥ ወዳለው ፍራቻ፣ የእምነት እርግጠኝነት፣ እውነተኝነት፣ ኢኽላስ (ፍፁማዊነት) ወይም የይዩልኝ ፣ የይስሙልኝ አስተሳሰብን ነው የሚመለከተው። ወደ ስራዎቻቸው ከመስተካከሏና ከመበላሸቷ አንፃር ይመለከትና በዛም መሰረት ይመነዳል።
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ ከዕለታት አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሳለን ድንገት ልብሱ እጅግ በጣም ነጭ የሆነ፤ ፀጉሩ ደግሞ እጅግ በጣም ጥቁር የሆነ ሰውዬ ብቅ አለ። በሱ ላይ የጉዞ ምልክት አይታይበትም፤ ከኛ ውስጥም አንድም የሚያውቀው ሰው የለም፤ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጥቶ ተቀመጠ። ጉልበቱን ወደ ጉልበታቸው አስጠጋ፤ መዳፎቹንም በታፋዎቹ ላይ አደረገና "ሙሐመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ!" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ኢስላም ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ልትመሰክር፣ ሰላት ደንብና ስርዓቱን ጠብቀህ ልትሰግድ፣ ዘካን ልትሰጥ ፣ ረመዷንን ልትፆምና ወደርሱ መንገድን ከቻልክም የአላህን ቤት ልትጎበኝ ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉት። እሱም "እውነት አልክ!" አላቸው። "በሱ ተገረምን ይጠይቃቸዋልም (ጥያቄውን በትክክል እንደመለሱ) ያረጋግጥላቸዋልም።" ከዚያም፦ "ስለኢማን ንገሩኝ!" አላቸው። እሳቸውም "በአላህ፣ በመላእክቱ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀንና በጥሩውም ሆነ መጥፎ ውሳኔዎቹም ልታምን ነው።" አሉት። እሱም "እውነት አልክ!" አላቸው። "ስለኢሕሳን (በጎ መስራት) ንገሩኝ!" አላቸው። እሳቸውም "አላህን ልክ እንደምታየው ሆነህ ልትገዛው ነው። አንተ ባታየው እንኳ እርሱ ያይሀልና።" አሉት። "ስለ ሰዓቱቱ (ቂያማ) ንገረኝ!" አላቸው። እሳቸውም "ስለርሷ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ አዋቂ አይደለም።" አሉት። "ስለ ምልክቶቿ ይንገሩኝ!" አለ። እሳቸውም "ባሪያ ጌታዋን ልትወልድ ነው ፤ ያልተጫማ፣ የታረዘ፣ ድሃና የፍየል እረኛ የሆኑ ሰዎች ለህንፃዎች ሲሽቀዳደሙ ማየትህ ነው።" አሉት። ዑመር እንዲህ አለ "ከዚያም ሄደ። የተወሰነ ጊዜ ቆየሁ። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ዑመር ሆይ! ጠያቂው ማን እንደነበር አውቀሀልን?" አሉኝ። እኔም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። እሳቸውም "እርሱ ጂብሪል ነው እምነታችሁን ሊያሳውቃችሁ መጥቷችሁ ነው።" አሉ።
ሙስሊም ዘግበውታል።ዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከዕለታት አንድ ቀን ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በሶሐቦች መካከል አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በማይታወቅ ሰው ተመስሎ እንደመጣ ይናገራሉ። ከዚህም ሰውዬ ባህሪዎች መካከል ልብሱ እጅግ የነጣና ፀጉሩም እጅግ የጠቆረ ነበር። በሱ ላይም ድካም፣ አቧራ፣ የፀጉር መንጨባረርና የልብስ መቆሸሽ የመሰሉ የጉዞ ምልክት አይታይበትም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ተቀምጠው ከነበሩ ታዳሚዎች መካከልም አንድም ሰው አላወቀውም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፊት እንደተማሪ አቀማመጥ ተቀመጠ። ስለ ኢስላምም ጠየቃቸው። እሳቸውም እስልምና ማለት ሁለቱን የምስክር ቃላት ማረጋገጥ፣ አምስቱ ሶላቶች ላይ መጠባበቅ፣ ለሚገባው ሰው ዘካ መስጠት፣ ረመዷንን ወር መፆም፣ የቻለ ሰው ግዴታ የሆነውን ሐጅ መፈፀም እንደሆነ ማዕዘናቶቹን በመጥቀስ መለሱለት። ጠያቂውም "እውነት አልክ!" አለ። ሶሐቦችም ከላይ ሲታይ አጠያየቁ አለማወቁን የሚጠቁም፤ ከዛ ደግሞ ትክክለኛ መልስ እንደተመለሰለት ማረጋገጡን በማስተዋላቸው ግራ ተጋቡ። ከዚያም ስለ ኢማን ጠየቃቸው። እሳቸውም እነዚህን ስድስት ማዕዘናት ማመንን የሰበሰበ መልስ መለሱለት። እነሱም:-አላህ በመኖሩ፣ በባህሪያቶቹ፣ መፍጠርን በመሰሉ ድርጊቶቹና በአምልኮም ብቸኛ መሆኑን ማመን፤ አላህ ከብርሃን የፈጠራቸው መላእክቶች የተከበሩ ባሮቹ መሆናቸውን፣ አላህን የማያምፁና በትእዛዙ የሚተገብሩ መሆናቸውን ማመን፤ እንደ ቁርኣን፣ ተውራት፣ ኢንጂልና ሌሎችም ከአላህ ዘንድ በመልክተኞች ላይ በወረዱ መጽሐፍት ማመን፤ የአላህን ሃይማኖት የሚያደርሱ በሆኑ መልክተኞች ማመን ከነሱም መካከል ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳና የመጨረሻቸው የሆኑት ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂም ወሰለምና ሌሎችም ነቢያቶችና መልክተኞች ይጠቀሳሉ። በመጨረሻው ቀን ማመን፤ እዚህ ውስጥም ከሞት በኋላ ያሉ በቀብርና በበርዘኽ ህይወት እንዲሁም የሰው ልጅ ከሞት በኋላ የሚቀሰቀስና የሚተሳሰብ መመለሻውም ወይ ወደ ጀነት ወይ ወደ እሳት መሆኑን ማመንንም ያካትታል። አላህ በቀደመ ዕውቀቱ መሰረት፣ ጥበቡ ባስፈረደው መልኩ በፍላጎቱ መሰረት ነገሮችን እንደወሰነና በጽሑፍም እንዳሰፈረ ማመን፤ ምድር ላይ የሚከሰቱትም በወሰናትና በፈጠራት ልክ መሆኑንም ማመን ነው። ከዚያም ስለ ኢሕሳን (ስራን ማሳመር) ጠየቃቸው። ኢሕሳን ማለት ልክ አላህን እያዩ እንደሆነ እያሰቡ አላህን መገዛት ነው። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ባይረጋገጥለት (ባይችል) እንኳ ልክ አላህ እርሱን እያየው እንደሆነ በማሰብ አላህን መገዛት ነው። የመጀመሪያው: የ "ሙሻሀዳህ" (አሏህን እያየህ እንደሆነ እያሰብክ የምታመልክበት) ደረጃ ነው እሱም የላቀ ደረጃ ነው። ሁለተኛው ደግሞ የ "ሙራቀባህ" (አሏህ እያየኝ ነው በሚል ሃሳብ የምታመልክበት) ደረጃ ነው። ከዚያም ሰዓቲቱ መቼ እንደሆነች ጠየቃቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰዓቲቱ መከሰቻ ጊዜ አላህ በእውቀቱ ብቸኛ ከሆነበት ጉዳይ አንዱ በመሆኑ ተጠያቂውም ይሁን ጠያቂው ከፍጥረቱ መካከልም አንድም እንደማያውቀው ገለፁ። ከዚያም ስለ ሰዓቲቱ ምልክቶች ጠየቃቸው። ከምልክቶቿ መካከል የጭን ገረዶችና ልጆቻቸው እንደሚበዙ ወይም የልጆች የእናቶቻቸውን ሐቅ አለመወጣታቸው እንደሚበዛ ይህም ከእናቶቻቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር ልክ ከባሪያ ጋር እንዳላቸው አይነት መስተጋብር እንደሚሆን፤ ለበግ እረኞችና ለድሆች በመጨረሻው ዘመን ዱንያ ተዘርግታላቸው በህንፃ ውበትና አሰራር እንደሚፎካከሩ ገለፁ። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠያቂው ጂብሪል እንደነበረና የመጣውም ይህንኑ ቀጥተኛ እምነት ለሶሐቦች ሊያስተምር እንደሆነ ተናገሩ።
ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹በዚህ በመመሪያችን ውስጥ ከርሱ (ከትእዛዛችን) የሌለን አዲስ ነገር የፈጠረ ሰው እርሱ (የፈጠረው አዲስ ነገር) ተመላሽ ነው።›" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። በሙስሊም ዘገባ "ትእዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው እርሱ (ሥራው) ተመላሽ ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር የፈጠረ ወይም ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃ ያልጠቆሙትን ስራ የሰራ ሰው በባለቤቱ ላይ ተመላሽ እንደሚሆንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት እንደማይኖረው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።
ከአቢ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ካለውና ከጠራው አላህ ባወሩት (ሐዲሠል ቁድሲይ) አላህ እንዲህ ብሏል: "ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ! ባሮቼ ሆይ! ከመራሁት በስተቀር ሁላችሁም ጠማማ ናችሁና ምራቻን ከኔ ጠይቁ እመራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! ካበላሁት በስተቀር ሁላችሁም ረሀብተኞች ናችሁና መብልን ከኔ ጠይቁ እመግባችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እኔ ካለበስኩት በስተቀር ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁና ልብስን ከኔ ጠይቁ አለብሳችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ በሌሊትም ሆነ በቀን ትሳሳታላችሁ። እኔ ደግሞ ሁሉንም ወንጀሎችን እምራለሁ። ስለሆነም ምህረትን ከኔ ፈልጉ እምራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ እኔን ጉዳትን ልትጎዱኝ አትችሉም። ጥቅምን ልትጠቅሙኝ ዘንድም አትችሉም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም ከናንተ መካከል እንደሚገኝ አንድ እጅግ አላህን ፈሪ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይጨምርም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም እንደ አንድ እጅግ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰው ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም በአንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ቢቆሙና ቢጠይቁኝ ለእያንዳንዱም የጠየቀኝን ብሰጠው መርፌ ባህር የገባች ጊዜ እንደምትቀንሰው ያህል ካልሆነ በቀር ይህ (መስጠቴ) እኔ ዘንድ ካለው (ሀብት) ምንም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ይህቺ ስራችሁ ናት ለናንተ አስቀምጥላችኋለሁ ከዚያም እራሷን እመነዳችኋለሁ። ምንዳውን መልካም ሆኖ ያገኘ አላህን ያመስግን ፤ ከዛ ውጪ ሆኖ ያገኘ ግን ከነፍሱ በስተቀር ማንንም እንዳይወቅስ።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ በደልን በነፍሱ ላይ እርም እንዳደረገና አንዱ አንዱን እንዳይበድል በደልን በፍጡራኑ መካከልም እርም እንዳደረገው መናገሩን አብራሩ። ሁሉም ፍጡራን በአላህ መምራትና መግጠም ካልሆነ በቀር ከእውነተኛው መንገድ የጠመሙ ናቸው። መመራትን ከአላህ የጠየቀ ሰው አላህም ይገጥመዋል ይመራዋልም። ፍጡራን በሁሉም ጉዳዮቻቸው ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸው። አላህን የጠየቀን ሰው አላህም ጉዳዩን ይፈፅምለታል ይበቃዋልም። ፍጡራን ሌት ተቀን ወንጀል ይፈፅማሉ። አላህ ደግሞ ባሪያው ምህረትን በሚጠይቀው ወቅት ይሸሽገዋልም ያልፈዋልም። ፍጡራን አላህን አንዳችም ሊጎዱም ወይም ሊጠቅሙ አይችሉም። ፍጡራን ሁሉ እንደ አንድ አላህን እጅግ የሚፈራ ቀልብ ያለው ግለሰብ ቢሆኑ ፍራቻቸው በአላህ ንግስና ላይ አትጨምርም። ሁሉም እንደ አንድ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑም ጥመታቸው በንግስናው ላይ አንዳችም አይቀንስም። ምክንያቱም ደካሞችና ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸውና። በሁሉም ሁኔታ፣ ዘመንና ስፍራ ወደርሱ ፈላጊዎች ናቸው። የተብቃቃም እሱ ብቻ ነው። ፍጡራን ሁሉ ሰዉም ጋኔኑም ከመጀመሪያቸው እስከመጨረሻቸው አላህን ለመጠየቅ በአንድ ስፍራ ላይ ቢቆሙና ከነርሱም ለእያንዳንዱ ሁሉ የጠየቀውን ቢሰጥ ይህ መስጠቱ አላህ ዘንድ ካለው አንዳችም አይቀንስም። ልክ እንደ መርፌ ባህር ውስጥ ገብታ ብትወጣ ባህሩ በዚህ አንዳችም እንደማይቀነሰው ማለት ነው። ይህም የሆነው ከተሟላው ሀብቱ አንፃር ነው። ጥራት ተገባው! ጥራት የተገባው አላህ የባሮችን ስራዎች ይጠብቃልም ያስቀምጣልም። ከዚያም እሷኑ የትንሳኤ ቀን ይመነዳቸዋል። የስራውን ምንዳ መልካም ሆኖ ያገኘው ሰው አላህ ትእዛዙን ለመፈፀም ስለገጠመው አላህን ያመስግን። የስራውን ምንዳ ከዚህ ውጪ ሆኖ ያገኘ ሰውም ወደ ክስረት የመራችውን በመጥፎ የምታዘው ነፍሱን እንጂ ሌላን እንዳይወቅስ።
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: አንድ እለት ከአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኋላ ሳለሁ እንዲህ አሉኝ "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁኝ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል፤ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ ፅፎብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ጽሑፉም ደርቋል።"
ቲርሚዚ ዘግበውታል።ኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር እየጋለበ ሳለ ለሱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል : እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮችን አሳውቅሀለሁ። አላህ ትእዛዙንና ወደርሱ መቃረቢያን እየፈፀምክ በሚያገኝህ ሁኔታና ወንጀልና ሀጢዐቶች ውስጥም በማያገኝህ ሁኔታ የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውንም በመራቅ አላህን ጠብቅ! ይህንን ከፈፀምክ ምንዳህ በዓለማዊም በአኺራዊም ጣጣዎች የአላህ ጥበቃና ወደየትም ብትዞር የቸገረህን በመርዳት አላህም የሚጠብቅህ ይሆናል። አንዳች ነገር መጠየቅ የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር ማንንም አትጠይቅ! የጠያቂዎችን ልመና የሚቀበለው እሱ ብቻ ነውና። እገዛን የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር በማንም አትታገዝ! የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ላንተ ከፃፈልህ በስተቀር አንድም ጥቅም እንደማታገኝና የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን በመጉዳት ላይ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ ከወሰነብህ በስተቀር ባንተ ላይ አንድም ጉዳት እንደማይደርሱብህ አንተ ዘንድ እርግጠኝነት ይኑር! ይህንን ጉዳይ የላቀውና የተከበረው አላህ ጥበቡና እውቀቱ ባስፈረደው መልኩ ፅፏታልም ወስኗታልም። አላህ የፃፈው ነገርም አይለወጥም።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን እምቢ ይላል?" አሉ። እሳቸውም "እኔን የታዘዘኝ ጀነት ገባ ፤ እኔን ያመፀኝ ደግሞ በርግጥም እምቢ ብሏል።" በማለት መለሱ።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት ከመግባት ራሱን ያቀበ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ህዝባቸው ጀነት እንደሚገቡ ተናገሩ። ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ራሱን ከጀነት ያቅባል?" አሉ። እሳቸውም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም : "መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከተለና የታዘዘ ጀነት ገባ። ያመፀና ለሸሪዐ ታዛዥ ያልሆነ ሰው ግን በርግጥም በመጥፎ ስራዎቹ ጀነት ከመግባት ራሱን አቅቧል።" በማለት መለሱላቸው።
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።"
አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።የነርሱ መለዮ የሆነን እምነት ወይም አምልኮ ወይም ተለምዷዊ ነገርን በማድረግ ከከሀዲያን ወይም ከአመፀኞች ወይም ከደጋግ ህዝቦችም ጋር የተመሳሰለ ሰው ከነርሱ እንደሚመደብ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። ምክንያቱም በውጫዊ ማንነት ከነርሱ ጋር መመሳሰል በውስጣዊ ማንነት ከነርሱ ጋር ወደ መመሳሰል ያደርሳልና። ከሆኑ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በነሱ የመደነቅ ውጤት መሆኑ ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው። ቀስ በቀስም እነሱን ወደመውደድ ፣ ወደማላቅ፣ ወደነርሱ ጥገኛ ወደመሆን ያደርሳል። ይህም አላህ ይጠብቀንና ሰውዬውን በውስጣዊ አመለካከቱና አምልኮው ሳይቀር ከነርሱ ጋር ወደመመሳሰል ይጎትተዋል።