





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ ጥፋትን ስጠው!" ይላል።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፀሐይ በምትወጣበት ቀናት ሁሉ ሁለት መልአኮች ወርደው እንደሚጣሩ ተናገሩ። አንደኛቸው እንዲህ ይላል: አላህ ሆይ! አላህን ለመታዘዝ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለእንግዶቹ፣ ለበጎ አድራጎት ለሚሰጥ ሰው ምትኩን ስጠው፤ ካወጠው የተሻለ ተካለትም ባርክለትም። ሌላኛው ደግሞ "አላህ ሆይ! ከመስጠት የሚቋጥርን ጥፋትን ስጠው፤ ለሚገባቸው ከመስጠት ገንዘቡን የነፈገንም ገንዘቡን አውድምበት!" ይላል።
ከሰህል ቢን ሰዕድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የኸይበር ቀን እንዲህ አሉ: "ነገ ይህንን ባንዲራ አላህ በርሱ እጅ ድልን ለሚያጎናፅፍ፣ አላህና መልክተኛውን ለሚወድ፣ አላህና መልክተኛውም የሚወዱት ለሆነ ሰው እሰጠዋለሁ።" ሰዎችም ለማን ነው የሚሰጠው? በሚል ሌሊታቸውን ተጠምደውበት አደሩ። ሰዎችም ያነጉ ጊዜ ሁሉም ባንዲራው እንዲሰጠው ተስፋ በማድረግ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ማልደው ሄዱ። እርሳቸውም "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ የት አለ? አሉ። ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አይኑን አሞታል" ተባሉ። እርሳቸውም "ሰው ላኩበት!" አሏቸው። እርሱም ተይዞ መጣና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዓይኑ ላይ ተፉና ዱዓ አደረጉለት። እርሱም ከዚህ በፊት ምንም በሽታ እንዳልነበረበት ሆኖ ተፈወሰ። ባንዲራውንም ሰጡት። ዐሊይም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንደኛው አምሳያ እስኪሆኑ ድረስ ልዋጋቸውን?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም አሉት: "ቀያቸው እስክትሰፍር ድረስ ተረጋግተህ ተጓዝ። ቀጥሎ ወደ እስልምና ጥራቸው። በነርሱ ላይ ግዴታ የሚሆንባቸውንም የአላህ ሐቅ ንገራቸው። በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ሙስሊሞች በኸይበር አይሁዶች ላይ በማግስቱ ድልን እንደሚጎናፀፉ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶሐቦች ነገሯቸው። ይህም እሳቸው ባንዲራ በሚሰጡት ሰው እጅ ነው። ይህም (ባንዲራ) ሰራዊቶች ለምልክትነት የሚይዙት አርማ ነው። ባንዲራው የሚሰጠው ሰው ባህሪም አላህና መልክተኛውን ይወዳል፣ አላህና መልክተኛውም ይወዱታል። ሶሐቦችም ይህንን ትልቅ ክብር በመፈለግ ባንዲራውን ስለሚሰጠው ሰው ማንነት ሲያወጉ ሌሊታቸውን ተጠምደውበት አደሩ። በማግስቱም ሁሉም ይህን ክብር መጎናፀፍን ተስፋ በማድረግ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሄዱ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ጠየቁ። አይኖቹን እንደታመመ ነገሯቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደርሱ ሰው ላኩና ይዘውት መጡ። ከተከበረው ምራቃቸውም በዐሊ አይኖች ላይ ተፉና ዱዓ አደረጉለት። ምንም በሽታ እንዳልያዘው ሰው እስኪመስል ድረስ ከበሽታው ተፈወሰ። ባንዲራውንም ሰጡትና የጠላት ምሽግ እስኪቀርብ ድረስ በእርጋታ እንዲጓዝ አዘዙት። በነርሱ ላይም ወደ እስልምና እንዲገቡ ጥሪ እንዲያቀርብላቸው፤ እስልምናን ከተቀበሉት በነርሱ ላይ ያለባቸውን ግዴታ እንዲነግራቸው አዘዙት። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ አላህ የመጣራት ትሩፋቱ አንድ ተጣሪ ለአንድ ሰው መመራት ሰበብ ከሆነ ይህ ለርሱ ዐረቦች ዘንድ ውድ ንብረት የሚባለውን ቀይ ግመል ከሚኖረው ወይም ኑሮት ሰደቃ ከሚሰጠው የበለጠ የተሻለ መሆኑን ለዐሊይ ገለፁለት።
ከዘይድ ቢን ኻሊድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ለሚዘምት ሰው መሳሪያ፣ መጓጓዣ፣ ምግብ፣ ቀለብና ሌሎችም ለጉዞው የግድ የሚያስፈልገውን ነገር ያሰናዳ ሰው ልክ እንደዘማቹ እንደሚቆጠርና የዘማቾቹን ምንዳ እርሱም እንደሚያገኝ ተናገሩ። የዘማችን ጉዳይ በመልካም ሊሸፍን ሃላፊነት የወሰደ ሰውና እርሱ (ዘማቹ) በራቀበት ወቅት ቤተሰቦቹን ሊንከባከብ የርሱን ቦታ የተተካ ሰውም ልክ እንደዘማች እንደሚቆጠር ተናገሩ።
ከየሕያ ቢን ዑማረህ አልማዚኒይ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ዐምር ቢን አቢ ሐሰን ለዐብደላህ ቢን ዘይድ ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዉዱእ አደራረግ ሲጠይቁ ተገኝቼ ነበር። ውሃ የያዘ እቃ እንዲመጣላቸው ጠየቁ። የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው። ከዉዱእ እቃው ውሃን ወደ እጃቸው በማፍሰስ ሶስት ጊዜ እጃቸውን አጠቡ። ቀጥሎ እጃቸውን ወደ እቃው በመክተት ሶስት ጊዜ ውሃ እየዘገኑ ተጉመጠመጡ፤ አፍንጫቸው ውስጥ ውሃ በመክተትም አወጡ። ቀጥሎ እጃቸውን በመክተት ሶስት ጊዜ ፊታቸውን ታጠቡ። ቀጥሎ ሁለት ጊዜ ሁለት እጃቸውን እስከ ክርኖቻቸው አጠቡ። ቀጥሎ እጃቸውን በመክተት ጭንቅላታቸውን አበሱ። እጃቸውን አንድ ጊዜ ወደኋላ ወስደው ወደፊት መለሷቸው። ቀጥሎ ሁለት እግሮቻቸውን እስከ ቁርጭምጭሚታቸው ድረስ አጠቡ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ዐብደላህ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ በተግባራዊ መልኩ ገለፁ። አነስ ያለ ውሃ የያዘ እቃ እንዲያመጣላቸው ጠየቁ። በመጀመሪያ ሁለት መዳፋቸውን በማጠብ ጀመሩ። እቃውን ዘንበል በማድረግ ውሃውን እያፈሰሱ ሁለት እጆቻቸውን ከእቃው ውጪ አድርገው ሶስት ጊዜ አጠቧቸው። ቀጥለውም እጃቸውን እቃ ውስጥ በመክተት ከርሱ ሶስት ጊዜ እየዘገኑ በያንዳንዱ መዝገን ተጉመጠመጡ አፍንጫቸውም ውስጥ ውሃ እየከተቱ አስወጡ። ቀጥሎ ከእቃው በመዝገን ሶስት ጊዜ ፊታቸውን አጠቡ። ቀጥሎ ከእቃው በመዝገን ሁለት እጃቸውን እስከ ክርናቸው ድረስ ሁለት ጊዜ አጠቡ። ቀጥሎ ሁለት እጃቸውን እቃ ውስጥ በመክተት ካረጠቡ በኋላ ጭንቅላታቸውን በሁለት እጆቻቸው አበሱ። ከጭንቅላታቸው ፊትለፊት በመጀመር ወደ ማጅራታቸው እስኪደርስ ድረስ አበሱ። ቀጥሎ ወደ ጀመሩበት ስፍራ እስኪደርስ ድረስ ሁለት እጃቸውን መለሷቸው። ቀጥሎ ሁለት እግሮቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው ጋር አጠቡ።
ከዓማር ቢን ያሲር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለአንድ ጉዳይ ላኩኝና የዘር ፈሳሽ ወጣኝ። ውሃ አላገኘሁምና እንስሳ መሬት ላይ እንደምትንከባለለው ተንከባለልኩኝ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣሁና ይህን ድርጊቴ አወሳሁላቸው። እርሳቸውም 'በእጅህ እንዲህ ብታደርግ በቂህ ነበር።' አሉና ከዚያም በሁለት እጃቸው መሬቱን አንድ ጊዜ መቱ። ከዚያም በግራ እጃቸው ቀኝ እጃቸውን አበሱ። የላይኛውን የመዳፋቸው ክፍልንና ፊታቸውን አበሱ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዓማር ቢን ያሲርን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለሆነ ጉዳይ ጉዞ ላኩት። በግንኙነት ወይም በተኛበት በስሜት የዘር ፈሳሽ በመውጣቱ ምክንያት ጀናባ አገኘው። የሚታጠብበት ውሃም አላገኘም። የሚያውቀው ዉዱእ ሲያጠፋ ለትንሹ ሐደሥ የሚደረገውን የተየሙም ብይን እንጂ ጀናባ ሲያጋጥም የሚደረገውን የተየሙም ብይን አያውቅም ነበር። ስለ አፈፃፀሙ ከተመራመረ በኋላ ዉዱእ ሲጠፋ የምድር ገፅ ላይ በሚገኝ አፈር ከፊል የዉዱእ አካላትን እንደሚታበሰው ለጀናባ የሚደረገው የተየሙም አፈፃፀም ደግሞ የግድ መላ ሰውነትን በአፈር ማዳረስ መሆን አለበት ብሎ አሰበ። ይህም በውሃ ቀይሶት ነው። ሰውነቱን ባጠቃላይ እንዲነካም አፈር ላይ ተንከባለለና ሰገደ። ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመጣ ጊዜም ትክክል ነው የፈፀምኩት ወይስ አይደለም? የሚለውን ለማወቅ ያደረገውን አወሳላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁለቱም ሐደሦች ማለት እንደሽንት ካለው ዉዱእ የሚያጠፋው ትንሹ ሐደሥ እና እንደ ጀናባ ካለው ገላ የሚያስታጥበው ትልቁ ሐደሥ የአፀዳድ አፈፃፀምን ገለፁለት። እርሱም በሁለት እጆቹ አንድ ጊዜ አፈርን በመምታት ከዚያም በግራ እጁ ቀኝ እጁን ያብሳል፤ የመዳፎቹን የላይኛውን ክፍልና ፊቱን ያብሳል።
ከጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን በመመስከር፣ ሶላትን በማቋቋም፣ ዘካን በመስጠት፣ መሪዎችን በመስማትና በመታዘዝ ላይ፣ ለሁሉም ሙስሊም ተቆርቋሪ (ታማኝ/ ቅን) በመሆን ላይ ቃል ኪዳን ተጋቧሃቸው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ሶሐቢዩ ጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ እንደነበርና እርሳቸውንም ቃልኪዳን እንደተጋባ ተናገረ። ቃል የተጋባውም በተውሒድ (አላህን በብቸኝነት በማምለክ)፣ በቀንና ምሽት አምስት ግዴታ የሆኑትን ሶላቶች ‐ መስፈርቶቿን፣ ማእዘናቶቿን፣ ግዴታዎቿንና ሱናዎቿን በማሟላት ‐ በመስገድ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ በመስጠት ላይ ‐ ዘካ: ግዴታ የሆነ ገንዘባዊ አምልኮ ሲሆን ከሀብታሞች ተወስዶ ለሚገባቸው ድሆችና ለሌሎችም የሚሰጥ ነው፣ ‐ መሪዎችን በመታዘዝ ላይ፣ ለሁሉም ሙስሊም ተቆርቋሪ (ቅን) በመሆን ላይ ‐ ይህም: ለሙስሊም ጥቅም በመጓጓት፣ መልካምን ለርሱ በማድረስ፣ በንግግርም ሆነ በተግባር መጥፎን ነገር ከርሱ በመከላከል ነው።
ከሙዓዝ ቢን ጀበል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።) ማለት ነው።
رواه أبو داود والنسائي وأحمدነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሙዓዝን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እጅ ያዙና ለርሱ እንዲህ አሉት: በአላህ እምልልሃለሁ እኔ እወድሃለሁ። ሙዓዝ ሆይ! በየሁሉም ሶላት መጨረሻ ላይ ይህን ማለት እንዳትተው አደራ እልሃለሁ። "አሏሁመ አዒኒ ዐላ ዚክሪከ" (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት አግዘኝ) ወደ አምልኮ የሚያቃርበኝ በሆነ ንግግርና ተግባር ሁሉ አግዘኝ። "ወሹክሪከ" ፀጋን በማግኘትና መከራን በማስወገድም (አንተን ለማመስገን) አግዘኝ። ለአላህ ስራን በማጥራትና ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል (አምልኮህን በማሳመርም) አግዘኝ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ እንዲህ ብሏል: ‹ሁሉም የአደም ልጅ ስራ ለርሱ ነው ፆም ሲቀር፤ ፆም ለኔ ነው። በርሱ የምመነዳውም እኔው ነኝ።› ፆም ጋሻ ነው። አንዳችሁ የፆም ቀኑ የሆነ ጊዜ ፀያፍ ቃልንም አይናገር አይጩህም። አንድ ሰው ከተሰዳደበው ወይም ከተጋደለው እኔ ፆመኛ ሰው ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የፆመኛ ሰው የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ ታውዳለች። ፆመኛ የሚደስትባቸው ሁለት ደስታ አሉት። ሲያፈጥርም ይደሰታል። ጌታውን የተገናኘ ጊዜም በመፆሙ ይደሰታል።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በሐዲሠል ቁድስ እንዲህ እንደሚል ተናገሩ:- ሁሉም የአደም ልጅ መልካም ስራ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ይነባበራል ፆም ሲቀር፤ ፆም ይዩልኝ የማይገባበት ስራ ነውና ለኔ ነው። እኔ ነኝ በርሱ የምመነዳው፤ የምንዳውን መጠንም ይሁን የአጅሩን መነባበር መጠን በማወቅ የተነጠልኩት እኔ ብቻ ነኝ። ቀጥለው (ፆም ጋሻ ነው) አሉ። ከእሳት የሚጠብቅ ጋሻ፣ መሸሸጊያና መጠበቂያ ነው። ፆም ወንጀል ላይ ከመውደቅ ስሜትን የሚያቅብ ነው። እሳት በስሜቶች የተከበበች ናትና። (አንዳችሁ የፆም ቀኑ የሆነ ጊዜ ፀያፍ ቃልን አይናገር) በግንኙነት ጉዳይም ይሁን ወደ ግንኙነት በሚያነሳሱ ነገሮች፤ በጥቅሉ የትኛውንም ፀያፍ ንግግር አይናገር። (አይጩህም) በክርክርና በጩኸት አይናገር። በረመዷን (አንድ ሰው ከተሰዳደበው ወይም ከተጋደለው) ከርሱ ሊቆጠብ ይከጀላልና እኔ ፆመኛ ሰው ነኝ ይበል። ሰውዬው ካልተጋደልኩ ብሎ ከደረቀ ሰው ሊያጠቃው ሲመጣ እንደሚያደርገው በቀላል መልኩ ይከላከለው። ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፆም ምክንያት የተለወጠ የፆመኛ አፍ ጠረን መዓዛው የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ‐እናንተ ዘንድ ካለው የሚስክ መአዛ የበለጠ‐ እንደሚያውድ፤ ምንዳው ደሞ በጁመዓና በዚክር መቀማመጥ ወቅት መቀባቱ ተወዳጅ ከሆነው ሚስክ የበለጠ ምንዳም እንደሚያስገኝ ነፍሳቸው በእጁ በሆነው ጌታ ምለው ተናገሩ። ፆመኛ የሚደሰትባቸው ሁለት ደስታዎች አሉት: በሚያፈጥር ወቅት ማፍጠሩ ተፈቅዶለት አፍጥሮ ረሃቡና ጥሙ በመወገዱ፣ ፆሙ በመሙላቱና አምልኮው በመጠናቀቁ፣ በጌታው ማቅለያና ለቀጣይ ፆሙ ማገዣ በመቅመሱ ይደሰታል። (ጌታውን የተገናኘ ጊዜም በፆሙ ይደሰታል።) በምንዳውና በክፍያው ይደሰታል።
ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ «በአንድ ምሽት የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከፍራሼ ላይ አጣኋቸው። በዳሰሳ ስፈልጋቸውም እጄ መስገጃቸው ላይ የተተከለችው የእግራቸው ውስጥ ላይ አረፈች። እርሳቸውም እንዲህ እያሉ ነበር " አላሁመ አዑዙ ቢሪዷከ ሚን ሰኸጢክ፣ ወቢሙዓፋቲከ ሚን ዑቁበቲክ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚንክ፣ ላኡሕሲ ሠናአን ዐለይክ አንተ ከማ አሥነይተ ዐላ ነፍሲክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከቁጣህ በውዴታህ፣ ከቅጣትህ በይቅር ባይነትህ እጠበቃለሁ፤ ከአንተ በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ እራስህን ያወደስከውን ያህል ላወድስህ አልችልም።" ማለት ነው።
ሙስሊም ዘግበውታል።ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ አለች "ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጎን ተኝቼ ነበር። ሌሊት ላይ አጣኋቸሁ። ቤት ውስጥ ይሰግዱበት የነበረውን ስፍራ በእጄ ዳሰስኩ። በዛን ጊዜም ሱጁድ ላይ ተደፍተው እግራቸውን ተተክለው አገኘሁ። እርሳቸውም እንዲህ እያሉ ነበር: (በውዴታህ) በኔ ላይም ይሁን በኡመቴ ላይ ከምትቆጣው (ቁጣህ) (እጠበቃለሁ) እቃረባለሁ። (ከቅጣትህ) ይቅር ባይነትህ ብዙ ነውና (በይቅር ባይነትህ) (እጠበቃለሁ)። (በአንተ ከአንተ እጠበቃለሁ።) ውብ በሆኑት ባህሪያትህ የልቅና መገለጫ ከሆኑት ባህሪያትህ እጠበቃለሁ። ከአንተ በቀር ከአንተ ለሚመጣው ቅጣት የሚጠብቅ የለምና። ወደ አላህ በመጠጋት ካልሆነ በቀርም ከአላህ መዳኛም መጠጊያም የለም። (በአንተ ላይ አወድሼ አልዘልቅም።) ፀጋህንና በጎ ውለታህን ቆጥሬ መዝለቅ ስለማልችል አንተ የሚገባህንም ውዳሴ በቁጥርም በገደብም ማወደሱን ብጥር እንኳ አልችልም። ለራስህ የሚገባውን በቂ ውዳሴ በራስህ ላይ ያወደስከው አንተ ብቻ ነህና (አንተ ነፍስህን ባወደስክበት ልክ ማወደስ አልችልም።) አንተን የማወደስ ሐቁን በአግባቡ መወጣት የሚችልስ ሌላ አካል ማን አለና?!