





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከዐሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሸሪዓዊ የምድር ቅጣት የተወሰነለትን ወንጀል የፈፀመና ቅጣቱም በዱንያ ተፈፃሚ የሆነበት ሰው አላህ በመጪውም አለም ባሪያውን በድጋሚ ከመቅጣት የላቀ ፍትሃዊ ነው። ሸሪዓዊ የምድር ቅጣት የተወሰነለትን ወንጀል የፈፀመ አላህም ለርሱ ምድር ላይ ሸሽጎለት ይቅር ካለው በኃላ አላህ ይቅር ያለውን አንዳች ነገር ወደ ኋላ ተመልሶ ከመቅጣትም የላቀ እጅግ ቸር ነው።"
ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደዝሙትና ስርቆት የመሰሉ ሸሪዓዊ የምድር ቅጣቶችን የሚያስፈርዱ ወንጀሎችን የፈፀመ ሰውና ቅጣቱን በምድር መቅጫ ሸሪዓው ህግ መሰረት የተቀጣ ይህ መቀጣቱ የተቀጣባትን ወንጀል እንደሚያብስለት፤ በመጪው አለም ያለበትንም ቅጣት እንደሚያስነሳለት ተናገሩ። ምክንያቱንም ሲገልፁ አላህ በባሪያው ላይ ሁለት ቅጣቶችን ሰብስቦ ከመቅጣት የላቀ አዛኝና ቸር ነው አሉ። አላህ በዱንያ ወንጀሉን የሸሸገለት፤ በዛ ወንጀሉም ያልቀጣው፤ አላህ ይቅር ያለውና የማረው ሰውም አላህ ዐዘ ወጀል የማረውንና ይቅር ያለውን ወንጀል ወደ ኋላ ተመልሶ ከመቅጣትም የላቀ የተከበረና ቸር ነው አሉ።
ከአማኞች እናት ከዓኢሻህ (ረዲየሏሁ ዓንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "በሩብ ዲናርና ከዛ በላይ በሚያወጣ (ስርቆት) እጅ ይቆረጣል።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአንድ ዲናር ሩብ እና ከዚህ በላይ የሚያወጣን ነገር የሰረቀ ሌባ እጁ እንደሚቆረጥ ገለፁ። ዋጋውም በንፁህ ወርቅ የ 1.06 ግራም ዋጋን ይመዝናል።
ከአቡ ቡርዳህ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ፦ "(አላህን በማመፁ ምክንያት) አላህ ያስቀመጠው የቅጣት ወሰን ካልሆነ በቀር (ስርአት ለማስያዝ) ተብሎ አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ እንዳይገረፍ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በወንጀል ላይ ካልሆነ በቀር አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ መገረፉን ከለከሉ። ሐዲሡ ውስጥ የተፈለገው በቁጥር ተገድበው ከአላህና ከመልክተኛው የመጡ ግርፋቶች ወይም ምቶች ወይም ልዩ ቅጣቶችን አይደለም። ይልቁንም በሐዲሡ የተፈለገው ስርአት ለማስያዝ ሲባል ሚስትንና ልጅን መግረፍ ቢያስፈልግ ከአስር አለንጋ አይጨምር ማለት ነው።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: «"ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።" ሳሊም እንዲህ አለ: አቡ ሁረይራም የእርሻ ባለቤት ነበርና "ወይም የእርሻ ጠባቂ ውሻ ካልሆነ" ይል ነበር።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለአደን ወይም ለከብቶችና አዝርዕት ጥበቃ ፈልጎ ካልሆነ በቀር ውሻን ከማሳደግ ከለከሉ። ከነዚህ ውጪ ለሆነ አላማ ያሳደገ ሰውም በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጥ ምንዳ ይቀነስበታል። ቂራጥ ሲባል የተፈለገው መጠንን የሚያውቀውም አላህ ብቻ ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ ገቡ። አንድ ሰውዬም መስጂድ ገባና ሰገደ። ነቢዩንም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱና እንዲህ አሉት "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" ቀደም ብሎ እንደሰገደው ለመስገድ ተመለሰ። ቀጥሎም በመምጣት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" እያሉት ሶስት ጊዜ ተመላለሰ። እርሱም "ያ በእውነት በላኮት ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" አላቸው። እርሳቸውም "ወደ ሶላት የቆምክ ጊዜ ተክቢራ አድርግ፤ ከዚያም ከቁርአን (ፋቲሓንና) የገራልህን ቅራ! ከዚያም በተረጋጋ ሁኔታ አጎንብስ፤ ከዚያም ቀጥብለህ በቆምክበት እስክትረጋጋ ድረስ ተነሳ፤ ከዚያም በሱጁድህ እስክትረጋጋ ድረስ ሱጁድ አድርግ፤ ከዚያም ተረጋግተህ እስክትቀመጥ ድረስ ተነሳ! በሁሉም የሶላትህ ክፍልም ይህንን ፈፅም።" አሉት።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ ገቡ። ከርሳቸው በኋላም አንድ ሰውዬ በመግባት በፍጥነት ሁለት ረከዓ ሰገደ። ይሁን እንጂ ሲቆምም፣ ሲያጎነብስም፣ ሱጁድ ሲወርድም እርጋታን አልተላበሰም ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶላቱን ይከታተሉት ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመስጂዱ አንድ ጎን ስር ተቀምጠው ሳለ ወደርሳቸው በመምጣት ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን ከመለሱለት በኋላ እንዲህ አሉት: አንተ አልሰገድክምና ተመለስና ሶላትህን ደግመህ ስገድ። ተመልሶም ቀደም ብሎ እንደሰገደው በፍጥነት ሰገደና ድጋሚ መጥቶ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታን አቀረበ። እርሳቸውም እንዲህ አሉት: አንተ አልሰገድክምና ተመልሰህ ስገድ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ፈፀመ። ሰውዬውም "በእውነት በላኮት ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" አለ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉት: "ወደ ሶላት የቆምክ ጊዜ የመክፈቻ ተክቢራ አድርግ፤ ከዚያም የቁርአን እናትን (ፋቲሓን)ና አላህ እንድትቀራ የሻልህን ቅራ፤ ከዚያም ባጎነበስክበት ሁኔታህ ላይ ሆነህ እስክትረጋጋ ድረስ አጎንብስ። ይህም መዳፎችህን ጉልበቶችህ ላይ በማድረግና ወገብህን በመዘርጋት ለሩኩዕህ በመመቻቸት ነው።፣ ከዚያም ቀና በል፤ አጥንቶችህ ወደ መገጣጠሚያቸው እስኪመለሱና ቆመህ እስክትስተካከል ድረስ ጀርባህን ቀጥ አድርግ፤ ከዚያም ሱጁድ ላይ ባለህበት ሁኔታ እስክትረጋጋ ድረስ ሱጁድ ውረድ። ይህም ግንባርን ከአፍንጫ ጋር፣ ሁለት እጆችን፣ ሁለቱ ጉልበቶችንና የሁለት እግሮች ጣቶችን ጫፍ መሬት ላይ በማመቻቸት በግንባር መደፋት ነው። ከዚያም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ተረጋግተህ እስክትቀመጥ ድረስ ከሱጁድህ መነሳት ነው። ከዚያም በሶላትህ በሁሉም ረከዓዎች ውስጥ ይህንን ፈፅም።"
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እጁን ሲታጠብም እንዲሁ እጆቹ እየዳሰሰች የፈፀመችው ኃጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እግሩን ሲታጠብም እንዲሁ እግሮቹ ስትራመድ የፈፀመችው ሀጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - ልክ እንደዚሁ እያለ ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ ከዉዱኡ እስኪወጣ ድረስ ከኃጢአቱ ይፀዳል።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ወይም ሙእሚን ዉዱእ ያደረገ ጊዜ በዉዱእ ሂደት ፊቱን ሲታጠብ በአይኖቹ የተመለከታቸው ትናንሽ ወንጀሎች ሁሉ ከታጠበ በኋላ ከሚወርደው ውሃ ጋር ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር ከፊቱ እንደሚራገፍ ገለፁ። እጆቹን የታጠበ ጊዜ ደግሞ እጆቹ የሰራቻቸው ሁሉም ትናንሽ ወንጀሎች ከውሃው ጋር ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር ከእጁ እንደሚራገፍ ገለፁ። ሁለቱን እግሮቹ የታጠበ ጊዜ ደግሞ እግሮቹ የተራመደችባቸው ሁሉም ትናንሽ ወንጀሎች ከውሃው ጋር ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር ከእግሩ እንደሚራገፍ ገለፁ። ይህም ውዱኡን ሲያጠናቅቅ ከትናንሽ ወንጀሎቹ ፀድቶ እስኪወጣ ድረስ ነው።
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የቁርአን ምዕራፍ እንደሚያስተምሩን ለጉዳያችን ኢስቲኻራን (አላህን የማማረጥን ዱዓ) እንዴት እንደምናደርግም ያስተምሩን ነበር። እንዲህም ይሉን ነበር: "አንዳችሁ አንድ ጉዳይ ያሰበ ጊዜ ግዴታ ከሆነ ሶላት ውጪ ሁለት ረከዓ ይስገድና እንዲህ ይበል: "አሏሁመ ኢኒ አስተኺሩከ ቢዒልሚክ ወአስተቅዲሩከ ቢቁድረቲክ ወአስአሉከ ሚን ፈድሊከል ዐዚም ፈኢንነከ ተቅዲሩ ወላ አቅዲር ወታዕለሙ ወላ አዕለሙ ወአንተ ዐላሙል ጙዩብ አሏሁመ ኢን ኩንተ ተዕለሙ አነ ሀዛል አምር ኸይሩን ሊ ፊ ዲኒ ወመዓሺ ወዓቂበቲ አምሪ" ወይም ደግሞ፡ "… አሏሁመ ኢን ኩንተ ተዕለሙ አነ ሀዛል አምር ኸይሩን ሊ ፊዓጂሊ አምሪ ወአጂሊሂ ፈስሪፍሁ ዓኒ ወስሪፍኒ ዓንሁ ወቅዱር ሊየል ኸይረ ሓይሡ ካነ ሡመርዲኒ" ይበል፤ ጉዳዩንም በስሙ ለይቶ ይግለፀው። አሉ።» (ትርጉሙም: "አላህ ሆይ! እኔ በዕውቀትህ አማርጥሃለሁ፣ በችሎታህ አቅምን እንድትሰጠኝ እጠይቅሃለሁ። ከትልቁ ችሮታህም እጠይቅሃለሁ። አንተ ትችላለህ እኔ አልችልም። አንተ ታውቃለህ እኔ አላውቅም። አንተ የሩቅን አዋቂ ነህ። አላህ ሆይ ይህ ጉዳይ ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬና ለጉዳዬ መዳረሻ ወይም ለቅርቡም ለወደፊቱም ጉዳዬ ለኔ መልካም መሆኑን ካወቅክ ለኔ ወስንልኝ አቅልልልኝም ከዚያም ለኔ በርሱ ባርክልኝ። ይህ ጉዳይ ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬና ለጉዳዬ መዳረሻ ወይም ለቅርቡም ለወደፊቱም ጉዳዬ ለኔ መጥፎ መሆኑን ካወቅክ ደግሞ ከኔ ዞር አድርግልኝም እኔንም ከርሱ ዞር አድርገኝ። መልካሙንም ካለበት ቦታ ወስንልኝ ከዚያም እንድወደው አድርገኝ።" ማለት ነው።»
ቡኻሪ ዘግበውታል።አንድ ሙስሊም ትክክሉ የቱ እንደሆነ የማያውቀው የሆነን ጉዳይ መፈፀም የፈለገ ጊዜ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦቻቸውን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የቁርአን አንድ ምዕራፍ እንደሚያስተምሯቸው ሁሉ ያስተማሯቸውን የነበረውን ይህንን ሶላት "ሶላተል ኢስቲኻራ"ን መስገድ ይደነገግለታል። ከግዴታ ሶላት ውጪ የሆነን ሁለት ረከዓ ይሰግድና ከዚያም አላህን እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጋል: "አልላሁመ ኢንኒ አስተኺሩከ" አላህ ሆይ! ከሁለቱ ጉዳዮች ለተሻለው እንድትገጥመኝ እፈልጋለሁ። "ቢዒልሚከ" ሁሉንም ነገር ባካባበው ሰፊ በሆነው እውቀትህም እጠይቅሃለሁ። "ወአስተቅዲሩከ ቢቁድረቲከ" በአንተ ካልሆነ በቀር ሀይልም ሆነ ብልሃት የለኝምና ፅኑ በሆነችው ችሎታህ ቻይ እንድታደርገኝ እጠይቅሃለሁ። አንተን ምንም አያቅትህምና። "ወአስአሉከ ሚንፈድሊከል ዐዚም" ሰፊ በሆነው በጎነትህ እጠይቅሃለሁ። የምትለግሰን ስጦታ ከአንተ የሆነ ችሮታ ነው። ለአንድም ሰው ፀጋህን የመዋል ግዴታ የለብህምና። "ፈኢንነከ ተቅዲር" አንተ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህና። እኔ ደግሞ ደካማ ነኝ። እኔ ደሞ "ወላአቅዲሩ" ያላንተ እገዛ አንድም ነገር ማድረግ አልችልም። "ወተዕለሙ" አንተ ውጫዊውንም ውስጣዊውንም፣ መልካሙንም መጥፎውንም ነገር አካባቢና ጠቅላይ በሆነ እውቀትህ ታውቃለህ። "ወላአዕለሙ" እኔ ደግሞ በአንተ መግጠምና መምራት ካልሆነ በቀር አንድም ነገር አላውቅም። "ወአንተ ዐላሙል ጉዩብ" አንተ የሩቅን አዋቂ ነህ። ጠቅላይ እውቀትና ፅኑ ችሎታ የአንተ ብቻ ነው። አንተ የወሰንክለትና ያስቻልከው ሰው ካልሆነ በቀር ከአንተ ውጪ ማንም ችሎታ የለውም። ቀጥሎ ይህ ዱዓ አድራጊ ሙስሊም ጉዳዩን እየጠቀሰ እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጋል። "አልላሁምመ" አላህ ሆይ! እኔ ጉዳዬን ወዳንተ አስጠግቻለሁ። "ኢንኩንተ ተዕለሙ" ስለዚህ ጉዳይ (ጉዳዩን በስሙ እየገለፀ) ባለህ እውቀትህ የምታውቀው ‐ ለምሳሌ:- ይህን ቤት መግዛቴ ወይም ይህን መኪና መግዛቴ ወይም ይህቺን ሴት ማግባቴ ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ወዘተ ይህ ጉዳይ ቀዳሚ በሆነው ዕውቀትህ "ኸይሩን ሊ ፊ ዲኒ" ለኔ የነገሮቼ መጠበቂያ ለሆነው ሃይማኖቴ የሚበጀኝ ከሆነ "ወመዓሺ" ለዱንያዬ ኑሮ የሚበጀኝ ከሆነ "ወዓቂበቱ አምሪ" ወደፊት ለሚያመራው ጉዳዬ ወይም እርሳቸው ያሉት "ፊ ዓጂሊ አምሪ ወአጂሊህ" ለዱንያዬም ሆነ ለመጪው አለሜ የሚበጀኝ ከሆነ "ፈቅዱርሁ ሊ" ወስንልኝ፣ አዘጋጅልኝ፣ ተፈፃሚ አድርግልኝ። "ወየሲርሁ ሊ ሡመ ባሪክ ሊ ፊህ" ለኔ አግራልኝ ከዚያም መልካሙን በማብዛትም ባርክልኝ። "ወኢንኩንተ ተዕለሙ" አላህ ሆይ! ስለጉዳዬ ባለህ እውቀት የምታውቀው "አንነ ሀዘል አምር" ይህ የማማርጥህ ጉዳይ "ሸሩን ሊ ፊ ዲኒ ወመዓሺ ወዓቂበቲ አምሪ" ወይም እርሳቸው ያሉት "ፊ ዓጂሊ አምሪ ወአጂሊህ ፈስሪፍሁ ዓኒ ወስሪፍኒ ዐንሁ ወቅዱር ሊ አልኸይረ ሐይሡ ካነ ሡመ አርዲኒ ቢህ" ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬና ለጉዳዬ መዳረሻ ወይም ለቅርቡም ለወደፊቱም ጉዳዬ ለኔ መጥፎ መሆኑን ካወቅክ ደግሞ ከኔ ዞር አድርግልኝም እኔንም ከርሱ ዞር አድርገኝ። መልካሙንም ካለበት ቦታ ወስንልኝ ከዚያም በምወደውም ሆነ በምጠላው ውሳኔዎችህ ባጠቃላይ እንድወደው አድርገኝ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።" አቡ ሰዒድም በዚህች ንግግር ተደሰተና እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በድጋሚ ይንገሩኝ!" እርሳቸውም ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉ: "ሌላም አንድ ስራ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ ይደረጋል። በየሁሉም ደረጃ መካከልም ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በአላህ ያመነና በጌትነቱ፣ በአምላክነቱ፣ በንጉስነቱ፣ በአለቃነቱ በአዛዥነቱ የወደደ፤ በእስልምና ሃይማኖትነት የወደደና በአጠቃላይ ትእዛዛቶችና ክልከላዎቹ የተመራና እጅ የሰጠ፤ በሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ነቢይነትና ይዘውት በመጡትና ባደረሱት ነገር ሁሉ የወደደ ሰው ጀነት ለርሱ ፀንታለታለች አሉት። አቡ ሰዒድም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዚህች ንግግር በመደሰት "ድገሙልኝ የአላህ መልክተኛ" አላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉት: "እኔ ዘንድ ሌላ ጉዳይ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ የሚደረግባት የሆነች፤ በየሁሉም ደረጃ መካከል ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" አቡ ሰዒድም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ቀን በጂሃድ ላይ እያለ የጾመ ሰው፤ ‐ በጂሃድም ሆነ ከዛ ውጪ እያለ የአላህን ምንዳና አጅር ፈልጎ ለአላህ አጥርቶ የፆመ ማለት ነውም ተብሏል። ‐ አላህ በችሮታው በርሱና በእሳት መካከል ሰባ ዓመታትን ያራርቃል ብለው ገለፁ።