





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: እውነተኛና (ይዘውት በመጡትም ሁሉ) እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን) ነገሩን፦ "የአንዳችሁ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀንና ምሽት ይሰበሰባል። ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ የረጋ ደም ይሆናል፤ ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ ቁራጭ ስጋ ይሆናል፤ ከዚያም ወደርሱ መልዐክ ይላካል ፤ መልዐኩ አራት መልእክቶች ይታዘዛል፤ ሲሳዩን፣ የሞት ቀጠሮውን፣ ስራውንና እድለቢስ ወይም እድለኛ መሆኑን ይጽፋል። ከዚያም በውስጡ ነፍስ ይነፋበታል። አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ውሳኔ) ይቀድምና የእሳት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል። አንዳችሁ በርሱና በእሳት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አለ፦ በንግግራቸው እውነተኛ የሆኑትና አላህ እውነተኛነታቸውን በማረጋገጡ እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነገሩን: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ፍጥረቱ ይሰበሰባል" ይህም አንድ ወንድ ባለቤቱን የተገናኘ ጊዜ የተበታተነው ዘር ፈሳሹ በሴቷ ማህጸን ውስጥ ለአርባ ቀን የዘር ፈሳሽ ሆኖ ይሰበሰባል። ከዚያም የረጋ ደም ይሆናል። ይህም የደረቀ ወፍራም ደም ነው። ይህ በሁለተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ቁራጭ ስጋ ይሆናል። ይህም የሚታኘክ የሚያህል ቁራጭ ስጋ ነው። ይህ በሶስተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ወደርሱ አላህ መልዐክ ይልካል። ሶስተኛው አርባ ከተጠናቀቀ በኋላ ፅንሱ ውስጥ ሩሕ (ነፍስ) ይነፋበታል። መልዐኩ አራት መልእክቶችን እንዲጽፍ ይታዘዛል። እነሱም:- ሲሳዩን: ይህም በእድሜው ውስጥ ምን ያህል መጠን ነው የሚያገኘው ፀጋ የሚለውን ነው። የሞት ቀጠሮውን:- ይህም በዱንያ ውስጥ የሚቆይበትን ዘመን ነው። ሥራውን:- ምንድነው እሱ? እድለቢስ ነው ወይስ እድለኛ? ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ማሉ። አንዱ የጀነት ሰዎችን ሥራ ይሠራል፤ ሥራው ለሰዎች በሚታየው መልካም ይሆናል፤ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል እስኪቀር በዚው መልክ ይቀጥላል። ማለትም አንድ ያሰበው ቦታ ለመድረስ አንድ ክንድ እንደቀረው ሰው በርሱና ጀነት በመግባት መካከልም አንድ ክንድ በስተቀር ምንም አይቀርም። በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና በዛን ወቅት የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና በዛው ላይ ፍፃሜው ይሆናል። እሳትም ይገባል። ሥራ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንዱ መስፈርት በዛው ላይ መፅናትና አለመለወጥ ነውና። ከሰዎች ሌላኛው ደግሞ እሳት ለመግባት በርሱና በእሳት መካከል የምድር አንድ ክንድ ያህል የቀረው እስኪመስል ድረስ የእሳት ባለቤቶችን ሥራ ይሠራል፤ በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።
ጣዉስ እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባለደረቦች የሆኑ ሰዎችን አግኝቻለሁ። "ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ ነው"ይሉም ነበር። ጣዉስ እንዲህም አሉ፦ " ዐብደላህ ቢን ዑመርን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ መሆኑን ገለፁ። ስንፍና ሳይቀር ተወስኗል: እሱም: - ዱንያዊና አኺራዊ ከሆኑ ጉዳዮች መስራት ግድ የሆነበትን ነገር መተው፣ ሳይሰሩ መገኘት ፣ ከወቅቱ ማዘግየት ነው። ጮሌነት ሳይቀር ተወስኗል: እሱም:- ዱንያዊና አኺራዊ ጉዳዮችን ለመስራት መነቃቃትና ብልህ መሆን ማለት ነው። የላቀውና የተከበረው አላህ ስንፍናና ጮሌነትን ሳይቀር ሁሉንም ነገር ወስኗል። በዚህ ዓለም የአላህ ዕውቀትና ፍላጎት የቀደመው ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አይከሰትም።
መጠር ቢን ዑካሚስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ አንድ ባሪያ በአንድ ቦታ እንዲሞት የወሰነ ጊዜ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድበትን ምክንያት ያደርግለታል።"
ቲርሚዚ ዘግበውታል።ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን፦ አንድ ባሪያ እሱ በማይኖርበት አንድ ስፍራ እንዲሞት አላህ የወሰነና የፈረደ ጊዜ ወደዛ ስፍራ የሚሄድበት ምክንያት (ጉዳይ) ያደርግበትና ይሄዳል። እዛም ስፍራ ላይ ነፍሱ ትያዛለች። በማለት ተናገሩ።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ መስጂድ ውስጥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። መስጂድ ውስጥ ግመሉን ካንበረከከ በኋላ አሰራት። ከዚያም ለነሱ እንዲህ አላቸው፦ "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመካከላቸው ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው። ለሳቸውም እንዲህ አላቸው "የዐብዱል ሙጠሊብ ልጅ ሆይ!" ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "አቤት ብያለሁ" አሉት። ሰውዬውም ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አላቸው፦ "እኔ እጠይቆታለሁ ስጠይቆት ጠንከር አደርግቦታለሁና ውስጦ በኔ ቅር እንዳይሰኝ።" እሳቸውም፦ "የፈለግከውን ጠይቅ!" አሉት። እሱም፦ "በአንተና ከአንተ በፊት ለነበሩት ጌታ በሆነው እጠይቅሀለሁ! አላህ ነውን ወደ ሰዎች ባጠቃላይ የላከህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። እሱም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን በቀንና በምሽት አምስት ሶላቶች እንድንሰግድ ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም ቀጥሎ "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ከአመት ይህንን ወር እንድንፆም ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም፦ "አዎን" አሉት። አሁንም በመቀጠል "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ይህንን ምፅዋት ከሀብታሞቻችን ወስደህ ለድሀዎቻችን እንድታከፋፍል ያዘዘህ?" አላቸው። እሳቸውም "አዎን" አሉት። ሰውዬውም፦ "ይዘውት በመጡት አምኛለሁ፤ ከኋላዬ ካሉ ህዝቦቼ የተላኩኝ መልክተኛ ነኝ። እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-፦ መስጂድ ውስጥ ሰሐቦች ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጋር ተቀምጠው ሳለ ድንገት አንድ ግመል ላይ ያለ ሰውዬ ገባ። ግመሉን ካንበረከከ በኋላም አሰራት። ከዚያም "ማንኛችሁ ነው ሙሐመድ?" በማለት ጠየቃቸው። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሰዎች መሀል ተደግፈው ነበር። "ይህ የተደገፈው ቀይ ሰውዬ ነው።" አልነው። ሰውዬውም ለርሳቸው፦ "የዐብዱል ሙጠሊብ ልጅ ሆይ!" አላቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለርሱ "ሰምቸሀለሁ ጠይቅ እመልስልሀለሁ።" አሉት። ሰውዬውም ለነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "እኔ እጠይቆታለሁ ስጠይቆት ጠንከር አደርግቦታለሁና ውስጦ በኔ ቅር እንዳይሰኝ።" አላቸው። ማለትም "በኔ እንዳይቆጡ በኔም መጨናነቅ እንዳያገኞት።" እሳቸውም፦ "የምትፈልገውን ጠይቅ" አሉት። እሱም "በእርሶና ከእርሶ በፊት ለነበሩት ጌታ በሆነው እጠይቆታለሁ! አላህ ነውን ወደ ሰዎች የላኮት?" አላቸው። እውነትነቱን ለማፅናት "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። ሰውዬውም፦ "በአላህ ስም እማፀኖታለሁ! አላህ ነውን በቀንና በምሽት አምስት ሶላቶች እንድንሰግድ ያዘዞት?" አላቸው። (ግዴታ ሶላቶችን) "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። "በአላህ ስም እማፀኖታለሁ! አላህ ነውን ከአመት ይህንን ወር እንድንፆም ያዘዘህ?" አላቸው። (ማለትም የረመዳንን ወር) "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። "በአላህ ስም እማፀንሀለሁ! አላህ ነውን ይህንን ምፅዋት ከሀብታሞቻችን ወስደህ ለድሀዎቻችን እንድታከፋፍል ያዘዘህ?" አላቸው። (ዘካ ለማለት ነው።) ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "አዎን በአላህ ይሁንብኝ" አሉት። ይህኔ ዺማም ሰለመ። ለነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ህዝቦቹን ወደ ኢስላም እንደሚጣራ ነገራቸው። ቀጥሎ ራሱን ከበኑ ሰዕድ ቢን በክር የሆነ ዺማም ቢን ሠዕለባህ እንደሆነ በመናገር አስተዋወቃቸው።
ዚያድ ቢን ለቢድ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ቁርኣን እየቀራን ፣ ልጆቻችንን እያቀራን፣ ልጆቻችንም ልጆቻቸውን እስከ እለተ ትንሳኤ እያቀሩ እንዴት ዕውቀት ይጠፋል?" አልኳቸው። እሳቸውም "እናትህ ትጣህ! ዚያድ በመዲና ጥልቅ ግንዛቤ ያለህ አድርጌ አይህ ነበርኩ። እነዚህ አይሁድና ክርስቲያን ተውራትና ኢንጂልን እየቀሩ ውስጣቸው ያለውን ምንም የማይሠሩ አይደሉምን?!" አሉኝ።
ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በባልደረቦቻቸው መሀል ተቀምጠው ሳለ እንዲህ አሉ፦ "ይህ ወቅት እውቀት ከሰዎች የሚነጠቅና የሚነሳበት ወቅት ነው።" ይህኔ ዚያድ ቢን ለቢድ አልአንሷሪይ በመደነቅ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጠየቁ። እንዲህም አሉ፦ "ቁርኣንን ቀርተነዋል፣ በቃላችን ሸምድደነዋል በአላህ እምላለሁ! እንቀራዋለን፣ ሴቶቻችንንም ልጆቻችንንም፣ የልጅ ልጆቻችንንም እያስቀራነው እንዴት ዕውቀት ይነሳል ከኛ እንዴት ይጠፋል?!" ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመደነቅ እንዲህ አሉ: "ዚያድ ሆይ! እናትህ ትጣህና ከመዲና ነዋሪዎች ውስጥ ከሚገኙ ዐሊሞች እቆጥርህ ነበርኩ።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሱ ዕውቀት የሚጠፋው ቁርኣን በመጥፋቱ እንዳልሆነ ነገር ግን ዕውቀት የሚጠፋው በዕውቀት መሥራት ሲጠፋ እንደሆነ አብራሩለት። ተውራትና ኢንጂል አይሁዶችና ክርስቲያኖች ዘንድ አለ። ከዚህም ጋር ምንም አልጠቀማቸውምም የታለመለትንም ግብ አላሳኩም። የታለመለት ዓላማ ባወቁት መሥራት ነበርና።
ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦ ቁርኣን የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አርባ ዓመታቸው ላይ ሳሉ ወረደ። በመካ አስራ ሦስት ዓመታት ቆዩ። ከዚያም በስደት ታዘዙ። ወደ መዲና ተሰደውም አስር ዓመታትን ቆዩ። ከዚያም ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አረፉ።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) በአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ የወረደውና የተላኩበት ዕድሜ አርባ መሆኑን፤ ከወሕይ መውረድ በኋላም በመካ አስራ ሶስት አመት መቆየታቸውን፤ ከዚያም ወደ መዲና እንዲሰደዱ እንደታዘዙና በመዲናም አስር አመታት እንደቆዩ፤ ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በስልሳ ሶስት አመታቸው እንዳረፉ ተናገሩ።
ቀታዳህ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደነገሩን አንድ ሰው "የአላህ ነቢይ ሆይ! ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀሳሉ?" አላቸው። እርሳቸውም " ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" አሉት። ቀታዳህ እንዲህ አሉ፦ "በጌታዬ ልቅና ይሁንብኝ እንዴታ!"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀላሉ?" ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው አላህ የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" በማለት መለሱ። አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአጎታቸው እንዲህ አሏቸው፦ " ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ" አቡ ጣሊብም "የቁረይሾች ማነወር ባልነበር "ለመስለም ያነሳሳው የሞት ፍራቻ ነው" ይላሉ ብዬ ባልሰጋ (እሰልም ነበር)" (ይህ ስጋት ባልነበር) ላ ኢላሀ ኢለላህ በማለት ደስታን አሰርፅልህ ነበር።" አላቸው። አላህም ይህን አንቀፅ አወረደ {አንተ የወደድከውን ሰው ፈፅሞ አታቀናም። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።} [አልቀሶስ: 56]
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አጎታቸው አቡ ጣሊብ ጣእረ ሞት ላይ ሳሉ ላኢላሀ ኢለላህን እንዲናገር ፈለጉ። ይህም የትንሳኤ ቀን በሷ ምክንያት ሊያማልዱትና በእስልምናው ሊመሰክሩለት ብለው ነው። አቡ ጧሊብ ግን ቁረይሾች እንዳይሰድቧቸው ፈርተውና "እርሱ የሰለመው ሞትና ደካማነትን በመፍራቱ ምክንያት ነው!" እንዳይባሉ በመስጋት የምስክርነት ቃሏን መናገር እምቢ አሉ። ለነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ይህ ስጋቴ ባልነበር የምስክር ቃሏን በመናገር በልብዎ ውስጥ ደስታን አስገባም ነበር እስኪደሰቱ ድረስም ምኞቶን አሳካ ነበር" አሏቸው። አላህም የፈለገውን ሰው እርሱ ብቻ እንጂ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኢስላምን በሰው ቀልብ ውስጥ በማስረፅ መምራት እንደማይችሉ የሚጠቁም አንቀፅ አወረደ። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፍጡራንን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በመጠቆም ፣ በማብራራት፣ በማቅናትና በመጣራት ነው የሚመሩት።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሣቢት ቢን ቀይስን አጡት። አንድ ሰውዬ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለርሱ ሁኔታ አጣርቼ አሳውቆታለሁ።" አለና ሣቢት ጋር ሲመጣ አንገቱን አቀርቅሮ ቤቱ ውስጥ ቁጭ ብሎ አገኘው። "ምን ሆነህ ነው?" አለው። ሣቢትም 'መጥፎ ነው' ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድምፅ በላይ ድምፁን ከፍ ያደርግ ነበር። ስራውም ተበላሽቶ ከእሳት ባለቤቶች ሆኗል።" አለው። ሰውዬውም መጥቶ ሣቢት ምን እንዳለ ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): " 'ወደርሱ ሂድና አንተ ከእሳት ሰዎች ሳትሆን ከጀነት ሰዎች ነህ በለው።' አሉት ሰውየውም ታላቅ የብስራት ዜና ይዞ በድጋሚ (ወደ ሣቢት) ተመለሰ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሣቢት ቢን ቀይስን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አጡትና ስለርሱ ጠየቁ። አንድ ሰውዬም "የጠፋበትን ምክንያት ለርሶ መረጃውን አገኝሎታለሁ።" በማለት ወደርሱ ሄደ። ቤቱ ውስጥ አዝኖ አንገቱን አቀርቅሮ አገኘው። "ምን ሆነህ ነው?" ብሎ ጠየቀው። ሣቢትም ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድምፅ በላይ ድምፁን ከፍ ያደርግ እንደነበር፤ አላህም ይህንን ያደረገ ሰው ስራው እንደተበላሸና የእሳት ባለቤት እንደሆነ በመናገሩ በርሱ ላይ የደረሰውን መጥፎ ነገር ነገረው። ሰውዬውም ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመመለስ ይህንን ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰውዬውን ወደ ሣቢት ተመልሶ ከእሳት ሰዎች እንዳልሆነ ነገር ግን ከጀነት ሰዎች እንደሆነ እንዲያበስረው አዘዙት። ይህም የሆነው የርሱ ድምፅ ከፍ ያለ መሆኑ ተፈጥሯዊ እና የነቢዩም የአንሷሮችም ኹጥባ አድራጊም ስለነበር ነው።