





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ የትንሳኤ ቀን ለሒሳብ ብሎ የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ ከአላህ ጋር ወይም ከሰዎች ጋር ሊሞላው ቃል የገባውን ቃል ኪዳን ላልሞላ ከዳተኛ ሁሉ ከዳተኝነቱ የሚጋለጥበት አርማ ይተከላል። በዛን እለትም በአርማው ላይ እንዲህ ተብሎ ይለፈፋል: "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የከዳው ክዳት ነው።" ይህም የትንሳኤ ቀን ለተሰበሰቡ ሰዎች መጥፎ ስራውን ለማሳየት ነው።
ከበራእ ቢን ዓዚብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰባት ነገር አዘዙን፤ ከሰባት ነገርም ከለከሉን። በሽተኛን በመጠየቅ፣ ጀናዛን በመሸኘት፣ ላስነጠሰ ዱዓ በማድረግ፣ መሃላን ወይም የማለን ሰው በማጥራት፣ ተበዳይን በመርዳት፣ የጠራንን ሰው ጥሪውን በማክበር፣ ሰላምታን በማስፋፋት አዘዙን፤ ከወርቅ ቀለበቶች ወይም የወርቅ ቀለበትን ከመልበስ፣ በብር እቃ ከመጠጣት፣ ከሐር የተሰራ ፎጣ ላይ ከመቀመጥ፣ (አልቀስሲይ) ከሐር ክር ተቀላቅሎ የተሰራን ልብስ ከመልበስ፣ ሐርን ከመልበስ፣ ከወፍራም ሐር የተሰራን ከመልበስ፣ ዲባጅ (ውዱን የሐር ጨርቅ) ከመልበስ ከለከሉን።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊሞችን በሰባት ነገሮች አዘዙ፤ ከሰባት ነገሮችም ከለከሏቸው። ያዘዟቸውም ነገሮች: የመጀመሪያው: በሽተኛን መጠየቅ ነው። ሁለተኛው: ጀናዛን መሸኘት፣ በርሱ ላይ መስገድ፣ መቅበርና ለርሱ ዱዓ ማድረግ ነው። ሶስተኛው: ላስነጠሰና አላህን ላመሰገነ ሰው "የርሐሙከሏህ" በማለት ዱዓ እንዲደረግለት ነው። አራተኛው: የማለን ሰው መሃላውን ማጥራትና ማረጋገጥ ነው። ማለትም በአንድ ጉዳይ ቢማልና አንተ መሃላው እውን እንዲሆን ማድረግ ከቻልክ ለመሃላው ማካካሻ ለማውጣት እንዳይገደድ የማለበትን ጉዳይ ፈፅም ማለት ነው። አምስተኛው: የተበደለን ሰው በማገዝ፣ በተቻለ መጠን በርሱ ላይ የሚደርሰውን በደል በመከላከል መርዳት ነው። ስድስተኛው: እንደሰርግ፣ ዐቂቃና ሌሎችም የምግብ ጥሪዎችን ለጠራ ጥሪውን ማክበር ነው። ሰባተኛው: ሰላምታ መስጠትንና ሰላምታን መመለስ ማስፋፋትና ማሰራጨት ነው። የከለከሏቸው ጉዳዮች ደግሞ: የመጀመሪያው: የወርቅ ቀለበት መልበስና በርሱ መዋብ ነው። ሁለተኛው: በብር እቃ መጠጣት ነው። ሶስተኛው: በፈረስና በግመል ኮርቻ ላይ በሚነጠፍ የሐር ፎጣ ላይ መቀመጥ ነው። አራተኛው: (አልቀስሲይ) ከተልባ እግር (ከበፍታ) እና ከሐር ተቀላቅሎ የተሰራን ልብስ መልበስ ነው። አምስተኛው: የሐር ልብስ መልበስ ነው። ስድስተኛው: በወፍራም ሐር የተሰራን ልብስ መልበስ ነው። ሰባተኛው: ዲባጅ መልበስ ነው። እርሱም: ከሐር አይነቶች መካከል ምርጡና ውዱ ነው።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአቡ ሱፍያን ባለቤት የሆነችው ሂንድ ቢንት ዑትባ የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ገባችና እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አቡ ሱፍያን ንፉግ ሰው ነው። ሳያውቅብኝ ከገንዘቡ ካልወሰድኩ በቀር ለኔና ለልጆቼ የሚበቃንን ወጪ አይሰጠኝም። በዚህ እኔ ላይ ወንጀል ይኖርብኛልን?" የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ላንቺና ለልጆችሽ የሚበቃሽን ከገንዘቡ በአግባቡ ውሰጂ!" አሏት።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ሂንድ ቢንት ዑትባ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለባሏ አቡ ሱፍያን ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጠየቀች። እርሱ በገንዘቡ ስስታምና ንፉግ ነበር። እርሱ ሳያውቅ በድብቅ ከገንዘቡ ካልወሰደች በቀር ለርሷና ለልጆቿ የሚበቃትን ወጪ አይሰጣትም ነበር። ይህን በማድረጓ ወንጀል ይኖርባት እንደሁ ጠየቀች። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ባያውቅ እንኳ በተለምዶ በቂ ነው ተብሎ የተለመደውን ያህል ላንቺና ለልጆቹ ከገንዘቡ ውሰጂ።" አሏት።
ከሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ ረዲየላሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ለአንድ ቀን በአላህ መንገድ ኬላ መጠበቅ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ አንዳችሁ ጀነት ውስጥ ያለው አለንጋ የሚያህል ቦታ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ ባሪያው በአላህ መንገድ ማልዶ መጓዙ ወይም አርፍዶ መጓዙ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊሞችን ከከሃዲያን ለመጠበቅ ስራውን ለአላህ አጥርቶ በሙስሊሞችና በከሃዲዎች መካከል ያለ ኬላ ላይ ጥበቃ እያደረጉ አንድ ቀንም ማሳለፍ ከዱንያና ውስጧ ካለው እንደሚበልጥ፤ አንድ ባሪያ ጀነት ውስጥ በአላህ መንገድ የሚታገልበት አለንጋ ያህል ቦታ ማግኘቱ ከዱንያና ውስጧ ካለው እንደሚበልጥ፤ ከቀኑ መጀመሪያ እስከ ዝሁር ድረስ ባለው ወይም ከዝሁር ወቅት እስከ ምሽት ድረስ ባለው ጊዜ በአላህ መንገድ አንድ ጊዜ የመጓዝ ምንዳና አጅር ከዱንያና ውስጧ ካለው እንደሚበልጥ ተናገሩ።
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡዱሒያ ሁለት ቡራቡሬና ቀንዳም የሆኑ ሙክቶችን በእጃቸው አረዱ። "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" አሉና እግራቸውን አንገቱ ላይ አድርገው አረዱት።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዒድ አልአድሓ ቀን በእጃቸው ሁለት ቀንዳሞችና ጥቁር የተቀላቀለባቸው ነጫጭ ወንድ ሙክት በጎችን "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" በማለት እግራቸውን አንገታቸው ላይ አድርገው እንዳረዱ ተናገረ።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "የሙስሊምን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ እየዋሸ የማለ ሰው አላህ በርሱ ላይ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል።" አሽዓሥም እንዲህ አለ: "በአላህ እምላለሁ! ይህንን የተናገሩት በኔ ምክንያት ነበር። በኔና በአንድ አይሁድ መካከል የመሬት ውል ነበረንና ካደኝ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድም ለፍርድ አቆምኩት። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ማስረጃ አለህን?" አሉኝ። እኔም "የለኝም።" አልኩኝ። ከዛም ለአይሁዱ "ማል።" አሉት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዲህ ከሆነማ ምሎ ገንዘቤን ይወስዳል።" አልኳቸው። አላህም {እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ ... } ሙሉ አንቀፁን አወረደ።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሚምለው ሰው ውሸቱን እንደሆነ እያወቀ በመሃላው የሌላን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ በአላህ መማልን አስጠነቀቁ። ይህ ሰውም አላህ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል። አሽዓሥ ቢን ቀይስም ረዲየሏሁ ዐንሁ የዚህን ንግግር ሰበብ ሲገልፅ እንዲህ አለ: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን የተናገሩት በኔና በአንድ አይሁድ ሰውዬ መካከል በመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ጭቅጭቅ ስለነበረን ነው። ወደ ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለመፋረድ ሄድን። ለአሽዓሥም እንዲህ አሉት: "የከሰስከው ነገር ላንተ እንዲፈረድ ማስረጃ ማምጣት አለብህ። ይህንን ካልቻልክ የከሰስከው ተከሳሽህ መሃላው ካልያዘው በቀር ላንተ ምንም መብት የለህም።" አሽዓሥም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዲህ ከሆነማ ይህ አይሁድ ሰውዬ ምንም ሳይገደው ምሎ ገንዘቤን ይወስዳል።" አላህም ይህንን ንግግር በቁርአን ለማረጋገጥ ይህንን አወረደ: {እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን የሚለውጡ} ትእዛዙ አማኞች አደራን እንዲወጡ እያዘዘ ነው። {በመሃሎቻቸውም (የሚለውጡ)} በውሸት በስሙ የሚምሉ {ጥቂትን ዋጋ} የዱንያን ስብርባሪ ለማግኘት {እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ዕድል የላቸውም።} ምንም ዕጣ የላቸውም። {በትንሳኤ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም።} የሚያስደስታቸውንና የሚጠቅማቸውን ንግግር አያናግራቸውም። ይልቁንም ይቆጣባቸዋል። {የትንሳኤ ቀን ወደነርሱ አይመለከትም።} የእዝነትና የበጎነት እይታን አይመለከታቸውም። {አያነፃቸውምም።} በመልካም እያወሳ አያነፃቸውም። ከወንጀልና ከርክሰትም በምህረቱ አያጠራቸውም። {ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው።} በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አላቸው።
ከራፊዕ ቢን ኸዲጅ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «በዙል ሑለይፋ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር ነበርን። ሰዎች ለረሃብ ተጋለጡ። ግመሎችና ፍየሎች በምርኮ አግኝተው ነበር።» ራፊዕ እንዲህ አለ: «ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች ኋላ ነበሩ። (እርሳቸውን ከመጠበቅ) ቸኮሉና አረዱ። ድስጥ ላይም ጣዱ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሲደርሱ ድስጡ እንዲደፋ አዘዙና ተደፋ። ከዚያም ምርኮውን አከፋፈሉ። የአስር ፍየልን ዋጋ በአንድ ግመል እያደረጉ አከፋፈሉ። አንድ ግመል ግን ፈረጠጠ። እርሱን ሲፈልጉም አደከማቸው። በመካከላቸው የነበረው የፈረስ ቁጥርም ትንሽ ነበር። ከመካከላቸው አንድ ሰውዬ በቀስቱ ወጋውና አላህ አቆመላቸው። ቀጥለው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "እነዚህ (የቤት) እንስሶች እንደ ዱር እንስሶች የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል አልያዝ ብሎ ያሸነፋችሁ ላይ እንደዚሁ አድርጉ።"» ራፊዕ እንዲህ ብሎም ጠየቃቸው: «እኛ ነገ ከጠላት ጋር እንገናኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን ወይም እንሰጋለን። የምናርድበት ቢላም የለንም። በተሳለ ቀርከሃ እንረድን? እርሳቸውም: "ከጥርስና ከጥፍር ውጪ ደምን ያፈሰሰና ሲታረድ የአላህ ስም የተወሳበትን ብሉ። የዚህንም ምክንያት እነግራችኋለሁ። ጥርስ የማታርዱበት አጥንት ስለሆነ ነው፤ ጥፍር የማታርዱበት ደግሞ የሐበሾች ስለት ስለሆነ ነው።" አሉ።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ራፊዕ ቢን ኸዲጅ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዙል ሑለይፋ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር እንደነበር ተናገረ። ሰዎችንም ረሃብ አጋጠማቸው። ከአጋርያን የማረኩት ፍየሎችና ግመሎች ነበሩ። ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሳያስፈቅዱም ምርኮ ከመከፋፈሉ በፊት ቸኮሉና አረዱ። ድስጥ ላይም ጣዱት። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች ኋላ ነበሩ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ያደረጉትን ሲያውቁ ድስጧ እንድትደፋ አዘው ከነመረቁ አስደፉት። ቀጥለው ምርኮዉን አከፋፈሉ። አስር ፍየሎችን በአንድ ግመል ተለዋጭ እያደረጉ አከፋፈሉ። ከነዚህ ግመሎችም አንድ ግመል ሸሸ። የነበራቸው ፈረስ ትንሽ ነበረና እርሱ ላይ መድረስ አቃታቸው። ከመካከላቸው የነበረ አንድ ሰውዬም በቀስት ወጋው። አላህም አቆመላቸው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "እነዚህ ለማዳ እንስሶችም የዱር ባህሪ አላቸው። ከነርሱ መካከል ለመያዝ ያቃታችሁና ያሸነፋችሁን እንደዚሁ አድርጉት።" ራፊዕም እንዲህ አለ: "እኛ ነገ ጠላትን እንገናኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በመሳሪያዎቻችን እንዳናርድ ስለቱን እንዳይጎዳብን ያሰጋናል። ማረዳችን ደግሞ ግድ ነው። እኛ ጋር ደግሞ ቢላ የለንምና በደረቀ ስለታማ ቀርከሃ እንረድን?" ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ከጥርስና ከጥፍር ውጪ ደምን አብዝቶ ያፈሰሰና ሲታረድ የአላህ ስም የተወሳበትን ብሉ። የሁለቱንም ምክንያት እነግራችኋለሁ። ጥርስ የማታርዱበት አጥንት ስለሆነ ነው። ጥፍር የማታርዱበት ደግሞ የሐበሻ ከሃዲዎች ለማረድ የሚጠቀሙበት ስለሆነ ነው።" አሉ።
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት ይገቡና እኔና የኔ እኩያ የሆነ ልጅም ውሃ የያዘ ዕቃና አንካሴ ተሸክመን እንወስድላቸው ነበር። በውሃውም እስቲንጃእ ያደርጉበት ነበር።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እርሱና የርሱ እኩያ የሆነ ሌላ አገልጋይ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ መፀዳጃ ቤት በሚሄዱበት ወቅት ይከተሏቸው እንደነበረና ከራሳቸው ጋርም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲፀዳዱ እርሱ ላይ አንድ ነገር አንጠልጥለው የሚከልሉበት ወይም ለሶላታቸው መከለያ የሚያደርጉት እንደጦር ጫፍ አምሳያ ጫፉ ላይ ሹልነት ያለውን ዘንግ እንደሚሸከሙ፤ በተጨማሪም ከቆዳ በተሰራ ትንሽዬ የውሃ መያዣ ውሃ ሞልተው ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደሚወስዱ ተናገረ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተፀዳድተው ሲጨርሱም ከሁለቱ አንዱ ውሃን ያቀብላቸውና በውሃው ኢስቲንጃእ እንደሚያደርጉ ተናገሩ።
ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ። ከርሳቸው ገሸሽ ስል "ቅረብ" አሉኝ። እግራቸው አጠገብ እስከምቆም ድረስ ቀረብኩ። ዉዱእ አደረጉና በኹፋቸው ላይ አበሱ።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ሑዘይፋ ቢን አልየማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መሽናት ፈለጉና የቆሻሻ መጣያ ስፍራ ገቡ። የአብዛኛው ጊዜ ልማዳቸው ተቀምጦ መሽናት ቢሆንም ቆመው ሸኑ። ሑዘይፋም ከርሳቸው ራቅ አለ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ቀረብ በል!" አሉት። ሑዘይፋም በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከእይታ ሊጋርዳቸው ከኋላቸው ተረከዛቸው አጠገብ እስኪቆም ድረስ ቀረባቸው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው ዉዱእ አደረጉ። እግራቸውን የሚታጠቡበት ቦታ ላይ ሲደርሱም ኹፋቸውን ሳያወልቁ በላዩ ላይ በማበስ ብቻ ተብቃቁ። ኹፍ ማለት ከቀጭን ቆዳ ወይም ከመሳሰሉት የሚሰራ እግር ላይ የሚጠለቅና እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ የሚለበስ ካልሲ ነው።