





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ ቀታዳ አስሰለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።በማንኛውም ወቅትና ለማንኛውም አላማ መስጂድ የመጣና የገባ ሰው ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ እንዲሰግድ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አነሳሱ። ይኸውም ሁለቱ የተሒየተል መስጂድ ረከዓዎች ናቸው።
ከአቡ ሑመይድ ወይም አቡ ኡሰይድ እንደተዘገበው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገባ ወቅት የሚባለውን ዱዓ ለኡመታቸው ጠቆሙ። (አልላሁምመ ኢፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲክ) (አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) የእዝነትን ምክንያቶች ለርሱ እንዲያመቻችለት አላህን ይጠይቃል። ከመስጂድ ለመውጣት የፈለገ ጊዜም (አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ) (አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል። አላህን ከችሮታውና ከሐላል ሲሳዩ ተጨማሪ ፀጋዎቹን ይጠይቃል።
ከሳሊም ቢን አቢ ጀዕድ እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: "አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: 'ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።' አለ። ሰዎቹ በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መስሎ ሲታይም እንዲህ አለ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'"
አቡዳውድ ዘግበውታል።ከሶሐቦች መካከል አንዱ "ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።" አለ። በዙሪያው ያሉ ሰዎች በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መሰሉ። በዚህ ጊዜም እንዲህ አለ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: 'ቢላል ሆይ! የሶላትን አዛንና ኢቃም አድርግ በርሷ እረፍት እንድናገኝ!'" ይህም ሶላት ውስጡ አላህን ማናገር፣ ለነፍስና ለቀልብ እርካታ ስላለው ነው።
ከአቡ ሐዚም ቢን ዲናር እንደተዘገበው: የተወሰኑ ሰዎች የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሚንበር ከምን አይነት እንጨት ነው የተሰራው? በሚለው ተከራክረው ሰህል ቢን ሰዕድ አስሳዒዲይ ዘንድ መጡ። ስለጉዳዩም ጠየቁት። እርሱም "ወላሂ እኔ ከምን እንደተሰራ አውቃለሁ። መጀመሪያ የተኖረበት ቀንና የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሱ ላይ መጀመሪያ የተቀመጡ እለት ተመልክቼዋለሁ። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ እከሊት (ከአንሷር የሆነች ሴት ስትሆን ሰህል ስሟን ጠርቷት ነበር።) "አናጢውን አገልጋይሽን ለሰዎች ንግግር ሳደርግ የምቀመጥበትን እንጨት እንዲሰራልኝ እዘዢ።" በማለት መልእክት ላኩላት። እርሷም አዘዘችው። እርሱም ሚንበሩን ‹ጦርፋኡል ጛባ› (ጠደቻ) ከሚባለው የእንጨት አይነት ሰርቶ ወደርሷ አመጣ። እርሷም ወደ አላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላከችው። በርሳቸው ትእዛዝም እዚህ ጋር ተቀመጠ። ከዚያም የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሱ ላይ ሲሰግዱበት ተመልክቻቸዋለሁ። ሚንበሩ ላይ እንዳሉ ተክቢራ አደረጉ ፣ እዛው ላይ እያሉም ሩኩዕ አደረጉ፣ ከዚያም ወደኋላ ወረዱ፣ ከሚንበሩ ስር ሱጁድ አደረጉና እንደገና ወደ ሚንበሩ ተመለሱ። ሶላቱን ያጠናቀቁ ጊዜ ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ 'እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት በኔ እንድትከተሉና አሰጋገዴንም እንድታውቁ ነው።'"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የተወሰኑ ሰዎች ወደ አንድ ሶሐባ የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር ሲያደርጉ የሚጠቀሙበት ሚንበር ከምን እንደተሰራ ሊጠይቁት መጡ። በዚህ ዙሪያም አየተነታረኩና እየተከራከሩ ነበር። ሱሓቢዩም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አናጢ አገልጋይ ወደነበራት የአንሷር ሴት "ለሰዎች ንግግር በማደርግበት ወቅት የምቀመጥበትን ሚንበር ለኔ እንዲሰራልኝ አገልጋይሽን እዘዢልኝ።" በማለት መልዕክተኛ መላካቸውን፤ እርሷም ትእዛዛቸውን በመቀበል አገልጋዩዋን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጦርፋእ ዛፍ ሚንበር እንዲሰራ ማዘዟን፤ ያጠናቀቀ ጊዜም ሚንበሩን ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መላኳን እርሳቸውም መስጂድ ውስጥ ቦታው ላይ እንዲቀመጥ አዘው መቀመጡንና ሚንበሩ ላይም መስገዳቸውን አወሳ። ሚንበሩ ላይ ሆነው ተክቢራ አደረጉ፣ እርሱ ላይ እንዳሉም ሩኩዕ አደረጉ፣ ከዚያም ፊታቸውን ወደኋላ አቅጣጫ ሳያዞሩ ወደኋላ እያፈገፈጉ በመውረድ ሚንበሩ ስር ሱጁድ ወረዱ፣ ከዚያም ወደ ሚንበሩ ተመለሱ። በዚህ መልኩ ሰግደው እንዳጠናቀቁም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህንን የፈፀምኩት እንድትከተሉኙና አሰጋገዴን እንድታውቁ ነው።"
ከሒጥጧን ቢን ዐብደሏህ አርረቃሺይ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ ጋር ሶላትን ሰገድኩ። ልክ ተሸሁድ ላይ የደረሱ ጊዜም ከሰዎች መካከል አንድ ሰውዬ 'ሶላት ከበጎነትና ከዘካ ጋር ተቆራኘች።' አለ። አቡ ሙሳ ሶላቱን አጠናቆ አሰላመተና ወደ ሰዎች በመዞር 'እንዲህ እንዲህ የሚል ንግግር የተናገረው ማነው?' አለ። ሰዎቹም ዝም አሉ። በድጋሚ 'እንዲህ እንዲህ የሚል ንግግር የተናገረው ማነው?' አለ። አሁንም ሰዎቹ ዝም አሉ። አቡ ሙሳም 'ሒጧን ሆይ! አንተ ነህ መሰለኝ ይህን የተናገርከው?' አለኝ። ሒጧንም 'እኔ አላልኩም! በሷ ምክንያት ትወቅሰኛለህ ብዬ እኔም ፈርቼ ነበር።' አለ። በዚህ ወቅት ከሰዎቹ መካከል አንድ ሰውዬ 'እኔ ነኝ ያልኩት። መልካምን እንጂ ሌላ አልፈለግኩበትም።' አለ። አቡ ሙሳም 'ሶላታችሁ ውስጥ እንዴት እንደምትሉ አታውቁምን? የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኹጥባ አደረጉ። ለኛ ሱናቸውን ገለፁልን አሰጋገዳችንንም አስተማሩን።' እንዲህም አሉን: ‹ሶላትን መስገድ የፈለጋችሁ ጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ። ከዚያም አንድ ሰው ይምራችሁ። ኢማሙ ተክቢራ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጉ! ፣ {غَيرِ المَغضوبِ عَلَيهِم وَلَا الضّالّينَ} [አልፋቲሐ:7] ያለ ጊዜ አሚን በሉ አላህ ይቀበላችኋልና፤ ተክቢራ አድርጎ ሩኩዕ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጋችሁ ሩኩዕ አድርጉ። ኢማሙ ከናንተ በፊት ሩኩዕ ያድርግ ከናንተ በፊትም ቀና ይበል።› የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህም አሉ "ይህቺ (ኢማሙ ቀና ያለበት ቅፅበት) በዚህች (እናንተ ከኢማሙ ከዘገያችሁበት) ጋር ይካካሳል ፤ ኢማሙ 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' ያለ ጊዜ 'አላሁመ ረበና ለከል ሐምድ' በሉ። አላህ ይሰማችኋልና። የጠራውና ከፍያለው አላህ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' 'አላህ ያመሰገነውን ሰሚ ነው' ብሏልና። ኢማሙ ተክቢራ አድርጎ ሱጁድ የወረደ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጋችሁ ሱጁድ ውረዱ። ኢማሙ ከናንተ በፊት ሱጁድ ይውረድ ከናንተ በፊትም ቀና ይበል። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህም አሉ 'ይህቺ (ኢማሙ ሱጁድ ሲወርድ የቀደማቹ ቅፅበት) በዚህች (እናንተ እርሱ ቀና ሲል በምትዘገዩት ቅፅበት) ይካካሳል።' የምትቀመጡበት በሆነ ወቅት የአንዳችሁ የመጀመሪያ ቃሉ 'አትተሒይያቱ፣ አጥጦይዪባቱ፣ አስሶለዋቱ ሊላሂ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢዩ ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ አስሰላሙ ዐለይና ወዐላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' ይሁን። ትርጉሙም 'ክብሮች ባጠቃላይ፣ ጥሩ ነገሮች ባጠቃላይ፣ ሶላቶች ባጠቃላይ ለአላህ የተገቡ ናቸው። አንቱ ነቢይ ሆይ ሰላም፣ የአላህ እዝነትና በረከቱ በርሶ ላይ ይሁን። ሰላም በኛ ላይና በአላህ ደጋግ ባሮች ላይም ይስፈን። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ። ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልዕክተኛው መሆናቸውንም እመሰክራለሁ።' ማለት ነው።›"
ሙስሊም ዘግበውታል።ሶሐቢዩ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሶላትን አሰገዱ። ተሸሁድ በሚባልበት ስፍራ ላይ የደረሱ ጊዜም ከኋላቸው ከሚሰግዱ ሰጋጆች መካከል አንዱ "ቁርአን ውስጥ ሶላት ከበጎነትና ዘካ ጋር ተቆራኘች።" አለ። አቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሶላቱን ባጠናቀቁ ጊዜ ወደ ተከታዮቹ በመዞር "ከመካከላችሁ 'ቁርአን ውስጥ ሶላት ከበጎነትና ዘካ ጋር ተቆራኘች።' ብሎ የተናገረው ማን ነው?" በማለት ጠየቋቸው። ሰዎቹም ዝም አሉ። ከነርሱ ውስጥ ማንም አልተናገረም። ጥያቄያቸውን ለሁለተኛ ጊዜ ደገሙት። አቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የሚመልስላቸው ያጡ ጊዜ ደፋርነቱን ስለሚያውቁ፣ ከርሳቸው ጋር ቅርርብና ትስስር ስላለው መጠርጠሩ በማያስከፋው መልኩ ትክክለኛውን ተናጋሪ ለማጋለጥ "ሒጧን ሆይ! አንተ ነህ መሰለኝ ያልከው?" አሉ። ሒጧንም አለመናገሩን በመግለፅ ከራሱ ላይ ለመከላከል እንዲህ አለ: "እኔም የተናገርኩ መስሎህ ትወቅሰኛለህ ብዬ ፈርቼ ነበር።" በዚህ ወቅት ከሰዎቹ መካከል አንዱ እንዲህ አለ "እኔ ነኝ ያልኩት መልካምን አስቤ እንጂ አልተናገርኩም።" አቡ ሙሳም እሱን እያወገዙ ለማስተማር እንዲህ አሉ: "ሶላታችሁ ውስጥ ምን እንደምትሉ አታውቁምን?" ቀጥለውም አቡ ሙሳ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ጊዜ ኹጥባ እንዳደረጉላቸውና ሸሪዓውን እንዳብራሩላቸው፣ ሶላታቸውንም እንዳስተማሯቸው ተናገሩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የሰገዳችሁ ጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ፣ ቀጥ በሉ ከዚያም ከመካከላቸው አንዱ ሰዎችን ይምራ። ኢማሙ የመክፈቻ ተክቢራ ያለ ጊዜ እንደርሱ አምሳያ ተክቢራ አድርጉ፤ ፋቲሐን የቀራ ጊዜና {غَيرِ المَغضوبِ عَلَيهِم وَلَا الضّالّينَ} [አልፋቲሐ:7] የሚለው ጋር የደረሰ ጊዜ አሚን በሉ ይህንን ከፈፀማችሁ አላህ ዱዓችሁን ይቀበላችኋልና፤ ኢማሙ ተክቢራ አድርጎ ሩኩዕ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጋችሁ ሩኩዕ አድርጉ። ኢማሙ ከናንተ በፊት ሩኩዕ ያደርጋል ከናንተ በፊትም ቀና ይላልና እንዳትቀድሙት። ኢማሙ ወደ ሩኩዕ ሲወርድ የቀደማችሁ ቅፅበት እናንተ ኢማሙ ቀና በሚልበት ቅፅበት ወቅት ሩኩዕ ላይ በመዘግየታችሁ ይካካሳል። ያቺ ቅፅበት በዚህች ቅፅበት ትካካሳለች። በዚህ የናንተም የሩኩዕ ቆይታ እንደርሱ የሩኩዕ ቆይታ ይሆናል። ኢማሙ 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' ያለ ጊዜ 'አላሁመ ረበና ለከል ሐምድ' በሉ። ሰጋጆች ይህንን ያሉ ጊዜ አላህ ዱዓቸውንና ንግግራቸውን ይሰማቸዋል። ምክንያቱም የጠራውና ከፍያለው አላህ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' 'አላህ ያመሰገነውን ሰሚ ነው' ብሏልና። ቀጥሎ ኢማሙ ተክቢራ አድርጎ ሱጁድ የወረደ ጊዜ ተከታዮቹም ተክቢራ አድርገው ሱጁድ መውረድ ይገባቸዋል። ኢማሙ ሱጁድ የሚወርደውም ሆነ የሚነሳው ከነርሱ በፊት ነውና። ያቺ ቅፅበት በዚህች ቅፅበት ትካካሳለች። የተከታዩ (የመእሙሙ) የሱጁድ መጠን እንደ ኢማሙ የሱጁድ መጠን ይሆናል። ለተሸሁድ የተቀመጠ ጊዜ የሰጋጅ የመጀመሪያ ቃሉ እንዲህ ማለት ይሁን: 'አትተሒይያቱ፣ አጥጦይዪባቱ፣ አስሶለዋቱ ሊላሂ'፤ 'ንግስና፣ ዘውታሪነትና ልቅና ሁሉ እንዲሁም አምስቱ ሶላቶችም ለአላህ የተገቡ ናቸው።' 'አስሰለሰሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢዩ ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ አስሰላሙ ዐለይና ወዐላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን' ከሁሉም ነውር፣ መከራ፣ ጉድለትና ብልሽት ሰላም እንዲያደርጋችሁ አላህን ተማፀኑ። ነቢያችንን ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሰላምታ ለብቻ እንነጥላቸዋለን። ከዚያም ከአላህ ሀቆችና ከባሮቹ ሀቆች ያለባቸው ግዴታዎችን በተወጡ የአላህ ደጋግ ባሪያዎች ላይም ሰላም እንዲሰፍን ዱዐ እናደርጋለን። ከዚያም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልዕክተኛው እንደሆኑ እንመሰክራለን።"
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: አቡ ሁረይራ ግዴታ ሶላቶችም ሆኑ ሱና ሶላቶች በረመዳን ውስጥም ሆነ በሌላ ወቅት በሁሉም ሶላቶች ሲሰግድ ተክቢራ ያደርግ ነበር። በሚቆም ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ሩኩዕ በሚያደርግ ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ሱጁድ ከመውረዱ በፊትም "ረበና ወለከል ሐምድ" "ጌታችን ላንተ ምስጋና የተገባ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም "አሏሁ አክበር" ይላል፤ ከዚያም ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ከሁለተኛው ረከዐ መቀመጥ በኃላ በሚነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል። ሶላቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ በየሁሉም ረከዐ ይህንን ይፈፅማል። ከዚያም በጨረሰ ጊዜ እንዲህ ይላል: " ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ጋር ለመመሳሰል እጅግ የቀረበውን ሶላት የምሰግድ ነኝ። ዱንያን እስኪለያዩ ድረስ ይህቺው ነበረች አሰጋገዳቸው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አሰጋገድ ባህሪ ከፊሉን ተናገሩ። እርሳቸው ወደ ሶላት የቆሙ ጊዜ ተክቢረተል ኢሕራም እንደሚያደርጉ፤ ቀጥለው ወደ ሩኩዕ በሚሸጋገሩ ጊዜ፣ ሱጁድ በሚያደርጉ ጊዜ፣ ከሱጁድ ራሳቸውን በሚያነሱ ጊዜ፣ ሁለተኛውን ሱጁድ በሚወርዱ ጊዜ፣ ከርሱም ራሳቸውን ቀና በሚያደርጉበት ጊዜ፣ ባለሶስት ወይም ባለአራት ረከዓ ሶላት ውስጥ ለመጀመሪያው ተሸሁድ ከተቀመጡ በኋላ ከሁለተኛው ረከዓ ሲነሱም ተክቢራ እንደሚያደርጉ፤ ቀጥለውም ሶላቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሁሉም የሶላቱ ክፍል ይህንን ይፈፅሙ እንደነበር ተናገሩ። ወገባቸውን ከሩኩዕ በሚያነሱ ጊዜም "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ይሉ ነበር። ከዚያም ከቆሙ በኋላ "ረበና ለከል ሐምድ" ይሉ እንደነበርም ተናገሩ። ከዚያም አቡ ሁረይራ ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ እንዲህ አሉ: ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እኔ የአላህ መልዕክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በማመሳሰል ከናንተ እጅግ የቀረብኩኝ ነኝ። ይህቺን አለም እስከሚለያዩ ድረስም የአሰጋገዳቸው ባህሪ ይህቺው ነበረች።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ከሚሰርቁ ሰዎች ሁሉ እጅግ መጥፎው ሶላቱን የሚሰርቅ ነው።› እርሱም ‹እንዴት ሶላቱን ይሰርቃታል?› አላቸው። እርሳቸውም ‹ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን ባለማሟላት።› ብለው መለሱለት።"
ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በስርቆት እጅግ በጣም መጥፎ ሰው ከሶላቱ የሚሰርቅ ሰው መሆኑን ገለፁ። ይህም ከዚህ ሌባ ተቃራኒ የሰውን ገንዘብ የወሰደ በዚህች አለም ሊጠቀምበት ይችል ይሆናል። ይህ ሌባ ግን ከራሱ የምንዳና አጅር ሐቅ የሚሰርቅ ነው። ሶሐቦችም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንዴት አንድ ሰው ከሶላቱ ይሰርቃል?" ብለው ጠየቁ። እርሳቸውም "ሩኩዑንም ሆነ ሱጁዱን አያሟላም።" ብለው መለሱ። ይህም በሩኩዑም በሱጁዱም ሲጣደፍ በተሟላ መልኩ እነርሱን አለመፈፀሙ ነው።
ከኢብኑ አቢ አውፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" ይሉ ነበር። ትርጉሙም "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው። አላህ ሆይ! ሰማያትን የሞላ፣ ምድርን የሞላ፣ ከነዚህም በኋላ ያሉ የፈለግከውን ነገሮችን የሞላ ምስጋና ላንተ የተገባ ነው።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" ይሉ ነበር። አላህን ያመሰገነ ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ ምስጋናውን ተቀብሎ ይመነዳዋል ማለት ነው። ከዚያም "አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" በሚለው ንግግራቸው ሰማያትን፣ ምድሮችን፣ በመካከላቸው ያለውን፣ አላህ የሻውን ነገርንም ሁሉ በሚሞላ ምስጋና አላህን ያመሰግኑ ነበር።
የሙጊራ ቢን ሹዕባ ጸሐፊ ከሆነው ወራድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ሙጊራ ቢን ሹዕባ ወደ ሙዐዊያህ የሚጻፍን እንዲህ የሚል ደብዳቤ አጻፈኝ: 'ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ እንዲህ ይሉ ነበር ‹ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላ የንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ› ትርጉሙም 'ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።'"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ "ላኢላሀ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ አላሁመ ላማኒዐ ሊማ አዕጦይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መነዕተ ወላየንፈዑ ዘልጀዲ ሚንከልጀድ" "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛና ለርሱ አጋር የሌለው ነው። ንግስናም ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ማንም ከልካይ የለውም። ለከለከልከውም ማንም ሰጪ የለውም። የክብር ባለቤትም ክብሩ ካንተ (ቅጣት) አያድንም።" ይሉ ነበር። ማለትም: የተውሒድ ቃል በሆነችው "ላኢላሀ ኢለሏህ" አረጋግጣለሁም አምናለሁም። ትክክለኛዋን አምልኮም ለአላህ አፅንቼ ከርሱ ውጪ ካሉ አካላቶችም ውድቅ አደርጋታለሁ። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም። እውነተኛውና የተሟላው ንግስና፣ የሰማያትና የምድር ባለቤቶችም ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ መሆኑን አረጋግጣለሁ። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። አላህ የወሰነው መስጠትም ይሁን መከልከል ማንም መላሽ የለውም። እርሱ ዘንድ የሀብት ባለቤት ሀብቱ አይጠቅመውም። ብቸኛ የሚጠቅመው መልካም ስራ ነው።