Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way






























Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሳቸው ላይ እየዋሸ እንደሆነ እያወቀ ወይም እየተጠራጠረ ወይም በአብዛኛው ግምቱ እየዋሸ እንደሆነ እየተሰማው ከርሳቸው ንግግርን ያስተላለፈና ያወራ ሰው ይህንን ውሸት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀጠፈው ጋር (በወንጀሉ) ይጋራል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሆን ብሎ ንግግርን ወይም ድርጊትን ወደርሳቸው አስጠግቶ በርሳቸው ላይ የዋሸ ሰው በመጨረሻው ዓለም በርሳቸው ላይ ለመዋሸቱ ምንዳ የእሳት መቀመጫ እንዳለው ገለፁ።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመጨረሻዎቹ ኡመታቸው ውስጥ ውሸትን የሚቀጥፉ ሰዎች ብቅ እንደሚሉ ተናገሩ። ከነርሱ በፊት አንድም ሰው ያልተናገረውን ይናገራሉ፤ የተዋሹና የተቀጠፉ ሐዲሦችን ይናገራሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከነርሱ እንድንርቅና እንዳንቀማመጣቸው፣ ከርሱ መራቅ እስኪያቅተን ድረስ ይህ የተቀጠፈ (የተፈበረከ) ሐዲሥ ነፍስ ውስጥ ተፅዕኖ እንዳያሳድርብንም ሐዲሣቸውን አለመስማትን አዘዙን።
ዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: ሁሉንም ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የምሰማውን ነገር በጽሑፍ መጠበቅ ፈልጌ እጽፈው ነበር። ከቁረይሽ የሆኑ ሰዎችም እንዲህ በማለት ከለከሉኝ "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰው ናቸው በቁጣና በደስታ ሰአትም ይናገራሉ፤ ሊሳሳቱም ይችላሉ።" እኔም ከመጻፍ ተቆጠብኩኝ። እነርሱ የተናገሩትን ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገርኳቸው። በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ እንዲህ አሉኝ: "ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በደስታም ይሁን በንዴት በማንኛውም ሁኔታ ላይ ብሆን ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።" በርግጥ ከፍ ያለው አላህም ስለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብሏል፦ {ከልብ ወለድም አይናገርም።* እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጂ ሌላ አይደለም።} [አንነጅም:3 -4]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢስላምን አምስት አስተማማኝ ምሶሶዎች እንደተሸከሙት ቤት አድርገው መሰሉት። የተቀሩት የኢስላም ጉዳዮች ደግሞ ቤቱን እንደሚያሟሉ ነገሮች ናቸው። ከእነዚህ ማእዘናት የመጀመሪያው: ሁለቱ የምስክርነት ቃላት ናቸው። እነርሱም: ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው። እነዚህ ሁለቱ የምስክርነት ቃላት እንደ አንድ ማእዘን ናቸው። አንዱ ከሌላኛው ተለይቶ የሚታይ አይደለምና። የአላህን ብቸኛ መሆንና ከርሱ ውጪ ያለውን ትቶ በብቸኝነት ለአምልኮ የተገባው እርሱ ብቻ መሆኑን በማመን፣ የሚያስፈርዱትን በመተግበር፣ በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልዕክተኝነታቸውን በማመንና እርሳቸውን በመከተል አንድ ባሪያ እነዚህን ሁለት የምስክርነት ቃላት ይናገራል። ሁለተኛው ማእዘን: በቀንና በምሽት የሚሰገዱ የሆኑት የፈጅር፣ የዙህር፣ የዐስር፣ የመጝሪብ እና የዒሻእ ሶላቶችን መስፈርቶቹን፣ ማእዘናቶቹንና ግዴታዎቹን ጠብቆ ማቋቋም ነው። ሶስተኛው ማእዘን: ግዴታ የሆነውን ዘካ ማውጣት ነው። ይህም ገንዘቡ በሸሪዓ የተወሰነውን ያህል መጠን የደረሰ ባለገንዘብ በሙሉ ለሚገባው አካል ሊሰጥ ግዴታ የተደረገበት ገንዘባዊ አምልኮ ነው። አራተኛው ማእዘን: ሐጅ ነው። እርሱም: አምልኳዊ በሆነ መልኩ የሐጅ ተግባራትን ለመፈፀም መካን ማሰብ ነው። አምስተኛው ማእዘን: ረመዷንን መፆም ነው። እርሱም: አላህን በማምለክ ኒያ ጎህ ከወጣችበት ሰአት ጀምሮ ፀሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ ከመብላት፣ ከመጠጣትና ሌሎችም ፆምን ከሚያስፈጥሩ ነገሮች መቆጠብ ማለት ነው።
ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አለ፦ በንግግራቸው እውነተኛ የሆኑትና አላህ እውነተኛነታቸውን በማረጋገጡ እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነገሩን: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ፍጥረቱ ይሰበሰባል" ይህም አንድ ወንድ ባለቤቱን የተገናኘ ጊዜ የተበታተነው ዘር ፈሳሹ በሴቷ ማህጸን ውስጥ ለአርባ ቀን የዘር ፈሳሽ ሆኖ ይሰበሰባል። ከዚያም የረጋ ደም ይሆናል። ይህም የደረቀ ወፍራም ደም ነው። ይህ በሁለተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ቁራጭ ስጋ ይሆናል። ይህም የሚታኘክ የሚያህል ቁራጭ ስጋ ነው። ይህ በሶስተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ወደርሱ አላህ መልዐክ ይልካል። ሶስተኛው አርባ ከተጠናቀቀ በኋላ ፅንሱ ውስጥ ሩሕ (ነፍስ) ይነፋበታል። መልዐኩ አራት መልእክቶችን እንዲጽፍ ይታዘዛል። እነሱም:- ሲሳዩን: ይህም በእድሜው ውስጥ ምን ያህል መጠን ነው የሚያገኘው ፀጋ የሚለውን ነው። የሞት ቀጠሮውን:- ይህም በዱንያ ውስጥ የሚቆይበትን ዘመን ነው። ሥራውን:- ምንድነው እሱ? እድለቢስ ነው ወይስ እድለኛ? ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ማሉ። አንዱ የጀነት ሰዎችን ሥራ ይሠራል፤ ሥራው ለሰዎች በሚታየው መልካም ይሆናል፤ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል እስኪቀር በዚው መልክ ይቀጥላል። ማለትም አንድ ያሰበው ቦታ ለመድረስ አንድ ክንድ እንደቀረው ሰው በርሱና ጀነት በመግባት መካከልም አንድ ክንድ በስተቀር ምንም አይቀርም። በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና በዛን ወቅት የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና በዛው ላይ ፍፃሜው ይሆናል። እሳትም ይገባል። ሥራ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንዱ መስፈርት በዛው ላይ መፅናትና አለመለወጥ ነውና። ከሰዎች ሌላኛው ደግሞ እሳት ለመግባት በርሱና በእሳት መካከል የምድር አንድ ክንድ ያህል የቀረው እስኪመስል ድረስ የእሳት ባለቤቶችን ሥራ ይሠራል፤ በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።
በሃይማኖት ውስጥ አዲስ ነገር የፈጠረ ወይም ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ማስረጃ ያልጠቆሙትን ስራ የሰራ ሰው በባለቤቱ ላይ ተመላሽ እንደሚሆንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት እንደማይኖረው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ነገር የከለከሉን ጊዜ ያለምንም መለየት ሁሉንም ክልከላዎች መራቅ በኛ ላይ ግዴታ እንደሆነና አንድ ነገር ያዘዙን ጊዜ ደግሞ የምንችለውን ያህል መስራት በኛ ላይ ግዴታ እንደሆነ ገለፁልን። ቀጥለውም እንደአንዳንድ የቀደሙ ህዝቦች አይነት አጠፋፍ እንዳንጠፋ አስጠነቀቁን። እነዚህ የቀደሙ ህዝቦች ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸውምና ጥያቄዎችን በማብዛታቸው አላህ በጥፋትና ውድመት አይነት ቀጣቸው። ስለዚህ እነርሱ እንደጠፉት እንዳንጠፋ እነደነርሱ ከመሆን መራቅ ይገባናል።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ መልካም፣ ከጉድለትና ነውር የጠራና የፀዳ፣ በምሉዕነት የሚገለፅ መሆኑን ተናገሩ፤ ከተግባርም፣ ከንግግርና ከእምነትም መልካም የሆነውን እንጂ እንደማይቀበል ተናገሩ። እርሱም ለአላህ ጥርት ተደርጎ የተሰራና የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ የተከተለ ስራ ነው። በዚህ ካልሆነ በቀርም ወደ አላህ መቃረብ አይገባም። ለአንድ አማኝ ስራው መልካም ከሚሆንበት ትላልቅ ነገሮች መካከል ምግቡ መልካም መሆኑ ነው። ይህም የተፈቀደውን መመገቡ ነው። በዚህም ስራው ይፀዳል። ስለዚህም የተፈቀደን በመብላትና መልካም በመስራት አላህ መልክተኞችን እንዳዘዘው ሁሉ አማኞችንም አዘዘ። አላህ እንዲህ አለ: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስሩ። እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝ።} እንዲህም አለ: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮችን ብሉ።} ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምንም ያህል ተቀባይነትን የሚያስገኙ ግልፅ ሰበቦችን ቢፈፅም ስራን የሚያበላሽና ተቀባይነቱን የሚያሳጣ ከሆነው ሐራም ምግብ ከመብላት አስጠነቀቁ። ለዱዓ ተቀባይነትን ያስገኛሉ ከተባሉት ግልፅ ሰበቦች መካከልም: የመጀመሪያ: እንደ ሐጅ፣ ጂሃድ፣ ዝምድናን መቀጠልና ከዚህም ውጪ ላሉ ነገሮች ለአምልኳዊ አላማዎች ጉዞን ማርዘም ነው። ሁለተኛው: ባለማበጠር ምክንያት የፀጉሩ መበታተንና በአፈር (በአቧራ) ምክንያት የልብሱ ቀለምና የሰውነት መልኩ መለወጡ ነው። ይህም አስገዳጅ ችግር የገጠመው መሆኑ ነው። ሶስተኛው: ወደ ሰማይ ዱዓ በማድረግ እጁን ከፍ ያደርጋል። አራተኛው: ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! እያለ ወደ አላህ በስሞቹ ይቃረባል፣ በዚህም ችክ ይላል። ከነዚህ ለዱዓ ተቀባይነትን ከሚያስገኙ ምክንያቶች ጋር ሆኖም ግን ዱዓው አልተሰማም። ይህም ምግቡ፣ መጠጡና ልብሱ ሐራም ስለሆነና በሐራም ስለተገነባ ነው። ባህሪው ይህ የሆነ ሰው ተቀባይነት ማግኘቱም ሩቅ ነው። አላህስ እንዴት ዱዓውን ይቀበለዋል?